You are here: HomeNEWS30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በቋሚ መልዕክተኞች ደረጃ ተጀምሯል - ኤፍ.ቢ.ሲ

30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በቋሚ መልዕክተኞች ደረጃ ተጀምሯል - ኤፍ.ቢ.ሲ

Published in Latest News
Rate this item
(0 votes)

ኢትዬ ዴሞክራሲ፣ አዲስ አበባ (ጥር 14፣ 2010) - ከ30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ አስቀድሞ የሚካሄዱ መደበኛ ስብስባዎች በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምረዋል።

 

በዛሬው እለትም 35ኛው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የህብረቱ ቋሚ መልዕክተኞች ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

 

የቋሚ መልእክተኞች ስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ፣ በህብረቱ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮችና ቋሚ መልዕክተኞች እንዲሁም የህብረቱ ኮሚሽነሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

 

ቋሚ መልዕክተኞቹ በሚያደርጉት ስብሰባ በመሪዎች ደረጃ ለሚካሄደው ጉባኤ የሚውል አጀንዳ የሚያዘጋጁ ሲሆን፥ ለመሪዎቹ ከመቅረቡ በፊትም በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በኩል የሚገመገም ይሆናል።

 

ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ የአፍሪካ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎም የመሪዎች ስብሰባ በይፋ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

 

የዘንድሮው ጉባኤ “ዘላቂ የፀረ-ሙስና ዘመቻ ለአፍሪካ ስር ነቀል ለውጥ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት ማብራሪያ፥ ኢትዮጵያ 30ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት አጠናቃለች።

 

አዲስ አበባ አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ከተማ እንደ መሆኗ ኗሪዎቿ ስብስባው ተጀምሮ እስከያልቅ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

 

በዚህ ጉባኤ ከ40 አገራት በላይ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት አቶ መለስ፥ ከህብረቱ አባል አገራት መሪዎች ባሻገር ከተለያዩ አገራት የሚመጡ መሪዎችም ጉባኤውን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

03161086
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
3006
4118
86599
75600
3161086

Since April 1, 2014

Photo Gallery