Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeNEWSዘመኑን በፍቅር መነሻ ስለፍቅር እንዋጀው

ዘመኑን በፍቅር መነሻ ስለፍቅር እንዋጀው Featured

Published in Latest News
Rate this item
(0 votes)

 

By Artist Solomon Tekalgn

ኢትዬጵያዊነትን አንስተው ንግግር ስላደመቁ አዲስ የሚፈጠር ማንነት ወይ ፍቅር ሊኖር አይችልም፡፡ በየትኛውም ዘመን መቼም ቢሆን ህዝቡ የሚያደርገውን ያውቃል፡፡

ዘመኑን በፍቅር መነሻ ስለፍቅር እንዋጀው ይህ ለዛሬው ጽሁፌ መነሻና መድረሻ መልእት ነው፡፡ ፍቅር በሚለው ጥልቅ ሰዋዊ ስሜት ለሁሉም የሰው ዘሮች የተሰጠ ጸጋ ቢሆንም ቅሉ በማሳያዎቹ እና በዋና ዋና መገለጫዎቹ ውስጥ ስናልፍ ግን ይሀ ስሜት እንደ ህዝብ ይበልጡኑ እኛ ኢትዬጵያዊያንን ከሌሎችም በላቀ መልኩ ይገልጸናል ብል አጋነንክ የሚለኝ ብዙ የሚኖር አይመስለኝም፡፡

በሩን ዘግቶ በሚኖር አለም ውስጥ የጎረቤት ቤት የራስ እስኪመስል ድረስ ከምግብ መጠጥ ባሻገር ሁሉም ማህበራዊ ትስስር የተጠናከረበት፡፡ የራስ ብቻ በሚባል ሃይማኖት በሚከወንበት አለም ውስጥ፣ ጦር በሚማዘዙ እምነት ተከታዬች በበዙባት አለም ውስጥ አንዱ የሌላውን በዓል ከማክበር ባሻገር አንዱ የሌላውን ቤተ እምነት እስከመገንባት የሚሄድባት ሃገር ኢትዬጵያ ነች፡፡

በቋንቋና ባህል፣ በወግና ልማድ ተመሳሳይ እና ተቀራራቢ መስተጋብር ብቻ ሳይሆን በመቻቻል የሚገለጽ ብዝሃነት ባለባት ሃገራችን ውስጥ ወና ዋና የሚባሉትን የፍቅር መገለጫዎች ሳይነገረን፣ ሳይጻፍ፣ ሳንሰበክ ለዘመናት ስንተገብር የኖርን ህዝቦች ነን ኢትዬጵያዊያን፡፡

በዚህ መስፈሪያ ፍቅር ውስጣችን የኖረ ቤተኛ ገንዘባችን እንጅ ከውጭ የምንቀበለው ወይም ተምረን የምንላበሰው እውቀት ሳይሆን ማንነታችን የሆነ ጸጋችን ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ካየነው ኢትዬጵያዊያን በህዝቦች ትስስር ውስጥ እንደው በያንዳንዱ ህዝባዊ እና መንግስታዊ ተግባር ውስጥ ይህንን የኖረ የህዝቦች መፋቀርና መተሳሰር ልናሳድቀው አሊያም የሆነ ሁነት እየፈጠርን ይበልጥ እውቅና ልንሰጠው እንችል ይሆናል እንጅ እንዳዲስ ልንፈጥረው አሊያም የፈጠርነው ያህል አድርገን ልንመጻደቅበት አሊያም ልናወራው አይገባም፡፡

በዚህ መንደርደሪያ ወደ ዋናው ነጥቤ ስሄድ ይህንን የኖረ የህዝቡን ትስስር ማጠናከር ተገቢ መሆኑን አምናለሁ፡፡ አንባቢዎቼ ይህንኑ ሃሳብ ትጋሩታላችሁ ብዬም አስባለሁ፡፡ ከዚህ አንጻር የአማራና የኦሮሞ አሊያም አማራና የትግራይ ህዝቦችን ስለፍቅር ማስተሳሰር በራሱ ችግር አለው የሚል መነሻ የለኝም፡፡

እዚህ ላይ ዋና ዋና ችግር ሆነው የሚመጡት ግን አንዱን ህዝብ ከሌላው ጋር ስለማፋቀር ሰራን ብለን ስንነሳ ሁለቱን ህዝቦች ምንም ተፋቅረው እንደማያውቁ አድርጎ መስበክ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ፍቅር አንደ ሱስ ድንገት እንዳገረሸባቸው አድርጎ ይህንን የመቀራረብ ሱስም አዲስ እንደተፈጠረ አድርጎ መሲህ መሆን ብዙ የሚያዋጣ አይደለም፡፡ በታሪክም በህሊናም ፍርድ ትልቅ ስህተት ላይ የሚጥል ነው፡፡

ሁለተኛው ትልቅ ስህተት የሚሆነው፣ ጉዳይ ሁለት ህዝቦችን ለማፋቀር አንድ ሌላ የሚጠላ ህዝብ ለመፈለግ የሚደረገው መኳተን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሁለት ህዝቦችን አፋቀርን ብሎ ሌላ አንድ ህዝብ እንዲጠላ በማድረግ ላይ መመስረት ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ የፍቅር መነሻው ፍቅር እንጅ ጥላቻ ከሆነ ጥልቅ ጥፋት መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ለዚህ መነሻ የሚሆነው ሌላውን ብሄር እንዲጠላ በማድረግ የሚፈጠር የፍቅር ጋብቻ እንደ ሃገር ህዝባዊ መነሻ የሌለው የጥፋት ጉዞ ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው “ዘመኑን በፍቅር መነሻ ስለፍቅር እንዋጀው” ያልሁት፡፡

በነገራችን ላይ አድማጮቼ እዚህ ላይ አንድ ሳይነሳ መታለፍ የሌበት ጉዳይ እንደ ህዝብ እኛ ጋር “የጠላቴ ጠላት ወዳቼ ነው” የሚለው አስተሳሰብ ወይም አባባል አይሰራም፡፡

አሊያም ደግሞ እንዲሁ በጋለ ስሜት ድንገት ብድግ ተብሎ የሚመሰረት ጋብቻ ወይም ፍች የለም፡፡ ምክንያቱም አማራው ከትግሬው አሊያም ከኦሮሞው ጋር ባንድ ዘመን ስርዓት ድንገት ብድግ ብሎ የሚፋቀርበት እና የሚጣለበት አጋጣሚ ሊኖር እንደማይችል ታሪክም ነባራዊ ሁኔታውም ይነግረናል፡፡

ጋብቻና ፍቺው በግለሰቦች እንደማህበረሰብም በኖረ እሴተ የሚቀጥል እንጅ መሪዎች ስለ ሱስ ምናምን ስለሰበኩ ብቻ የሚከናወን አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም ባለ ፕሮግራሜ እንደነገርኳችሁ መሪነት ማለት እንደ ፌስቡክ ባለገጽ ላይክ ለማግኜት የሚደረግ ሽሚያ ሳይሆን የህዝብን እሴት ባህልና ወግ ጠብቆ ህዝብን ለልማት የማስተባበር ጉዳይ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር አሁን አሁን እየሆነያለውን ሁኔታ ስንመለከተው አመራሩ እንደ አቢዬታዊ ዴሞክራት በህዝብ መሰረታዊ ጥቅሞች ላይ በትኩረት የሚሰራ ሳይሆን፣ እንደ ምእራባዊያኑ ባለሃብቱ እንደሚመራው ኔዎ ሌበራል ስርዓት ለግል ዝናና ክብር የሚሰራ አይነት እየሆነ ነው፡፡

ለዚህም ነው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችንም ሌላውን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን እርስ በእርስ በመከባበር እና በመተሳሰብ ላይ ተመስርቶ መቀጠል አለበት የምንለው፡፡ የአማራና የኦሮሞ ወንድማማችንት ፋሽን ሆኖ ሲወራ መስማት ለአንድ የሃገሩን ታሪክ ጠንቅቆ ለሚያውቅ ኢትዬጵያዊ የሚያሳምም ጉዳይ ነው፡፡ አድዋን በጋራ የተዋደቁ ህዝቦች ዛሬ ተጣልተው እንደኖሩ ህዝቦች አድርጎ ማሰብ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ እውነት ለመናገር ግዛቱን ለማስፋት እንደማንኛውም የፊውዳል ስርዓት አራማጅ ሰራዊት አዝምቶ ግፍ ሰራ በተባለው በሚኒሊክ ዘመን ሳይቀር አማራና ኦሮሞው ከመጋባት ከመተሳሰብ ያገዳቸው አንዳች የለም፡፡ በዚያው ስርዓት ደግሞ አማራና ኦሮሞው ከሌላው ህዝብ ጋር ሆነው በንጉሱ አዝማችነት ሃገራቸውን ከፋሽስት ወራሪ ታድገዋታል፡፡

እንዲህ ስርዓቱ ምንም ይሁን ምን አማራና ኦሮሞው አድዋ ላይ አብረው ከመዋደቅ ያገዳቸው አንዳች የለም፡፡ ዛሬም የክልል ፕሬዘዳንቶች ኢትዬጵያዊነትን አንስተው ንግግር ስላደመቁ አዲስ የሚፈጠር ማንነት ወይ ፍቅር ሊኖር አይችልም፡፡ በየትኛውም ዘመን መቼም ቢሆን ህዝቡ የሚያደርገውን ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው ያሁኑ የሁለቱን ህዝቦች ፍቅር ከመስበክ በዘለለ ጥላቻን በሌላው ላይ ማላዘን የለበትም የምንለው፡፡

ለዚህም ነው ህዝቡ የሚለውን የሚያዳምጥ አመራር ያስፈልጋል የሚባለው፡፡ ለዚህም ነው እንደ ምእራባዊያን መሪዎች ለዝና ሳይሆን ለህዝብ ፍላጎተ እንስራ የምንለው፡፡ በሳለፍነው ሳምንት የኦሮሚያን በአዲስ አበባ ላይ ልዬ ጥቅሙን አስመልክቶ በተዘጋጀው የፓርላማ መድረክ ላይ የሆነውን ከዚህ ለይቼ አላየውም፡፡

የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ጉዳይ ምን ያህል የውዝግብ አጀንዳ ሆኖ እንደከረመ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ በህገ መንግስቱ መሰረትም አዲስ አበባን በተመለከተ የተቀመጠ ቁም ነገር አለ፡፡ ህገ መንግስቱ አዲስ አበባን በተመለከተ የኦሮሚያን ልዬ ጥቅም መከበር እንዳለበት ደንግጓል፡፡

እዚህ ላይ ቀደም ባሉት ጊዜያት የተሳሰረ ልማት ለማምጣት የተደረገው ጥረት በነጃዋር መሪነት ወጣቱ በስሜት ያልተገባ አቋም እንዲይዝ በማድረግ  ሁከትና ግርግር እንዲፈጠር በማድረግ ልማት ሲደናቀፍ ስናስተውል ቆይተናል፡፡ እንግዲህ የትኛውም ልማት ይሁን በየትኛውም አካባቢ ይሰራ የሚጠቅመው ህዝቡን እስከሆነ ድረስ ስለምን ልማት ይደናቀፋል የሚጠቀመውስ ያካባቢው ህዝብ አይደለምን የሚል ጠያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡

እዚህ ላይ መልሱ ስለ ልማት ሳይሆን ስለ ጥፋት ብቻ የሚያወሩ መቀመጫቸውን ውጭ ያደረጉ አካላት ያደረጉት የቅስቀሳ ስራ ተሳክቶ ልማቱ ሲደናቀፍ ከርሟል፡፡ የቀደመውን ካሁኑ የተለዬ የሚያደርገው ግን አሁን ላይ እየተመከረበት ያለው እና ሊመከርበት የታሰበው የክልሉ እና የአዲስ አበባ ጉዳይ የውጭዎቹ ዝም ብለው ያገር ቤት ሹመኞች ፓርላማውን እንዳይመክር ማድረጋቸው ነው፡፡

ስለ ኢትዬጵያዊነት ሲያላዝን የነበረ የክልል አመራር ፓርላማው የህዝቡን አስተያየት ሊሰማ ባቀደበት ዋዜማ በፊስ ቡክ ገጹ ላይ ምክክሩን እንቃወም ብሎ ከጃዋር ያነሰ ጠቦ መታየት በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ በእለቱ ፓርላማ ገብቶ ክልላችን ስለ ጉዳዬ ባልተወያየበት ሁኔታ እዚህ መምከር አያስፈልግም ብሎ ማሳመጽ ምን ይባላል፡፡

በቀደም ጊዜ የህዝቤን ጥቅም ለማስከበር ቆርጫለሁ ያሉት አፈጉባኤው ራሳቸው ይህንን የፐብሊክ ሂሪንግ መስማት ግብዓት ይሆናል እንጅ የኦሮሚያን ህዝብ ጥቅም የሚነካ ውሳኔ የሚተላለፍበት አይደለም እያሉ ኢትዬጵያዊነትን አስመልክቶ ሲንግል የለቀቀውን ወጣቱን የክልል አመራር እንደሞገቱት ሰምተናል፡፡ ያ የክልሉ ነጋሪ የሆነው ሰው ግን የጋራ ጥቅምን በመቃወም እንዲያ መደንፋቱ ሁኔተውን አሳፋሪ አድርጎብኛል፡፡

ለዚህም ነው ካንገት በላይ የሚሰበክ ፍቅር መዳረሻወ ትስስር አይሆንም የምለው፡፡ እኛም ሆንን ህዝቡ የሚሆነውን ይታዘባል፡፡ አንዳንዴም ጃዋር ለምን ዝም አለ ለሚለው ጥያቄ መልስ ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም መነሻና መድረሻችን የህዝቡ ፍላጎትና እሴት ቢሆን ከከፋ ስህተት መራቅ እንችላለን፡፡ ዘመኑን በፍቅር መነሻ ስለፍቅር እንዋጀው፡፡

 

 

03040944
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1028
1650
42057
51980
3040944

Since April 1, 2014

Photo Gallery