You are here: HomeARTICLESየጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ምን የተለዬ ነገር አለው? እንዲህ አነጋጋሪ ያደረገውስ ምንድን ነው? ሰለሞን ተካልኝ

የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ምን የተለዬ ነገር አለው? እንዲህ አነጋጋሪ ያደረገውስ ምንድን ነው? ሰለሞን ተካልኝ

Published in Articles
Rate this item
(2 votes)

ጠቅላይ ምንስትር ሃይለማርያም በዚህ ሳምንት ፓርላማ ተገኝተዋል፡፡ ፓርላማው በአንክሮ የስድስት ወር የመንግስቱን አፈጻጸም እያደመጠ ነው፡፡ መንግስት እድገቱን 11 በመቶ ለማስቀጠል እየሰራ በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንዳለ ቀረበ፡፡
የመልካም አስተዳደር እና የኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የት እንደደረሰ እና በምን ሁኔታ እየሄደ እንዳለ ጠቅላይ ምንስትሩ አብራሩ፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ቀድሞ የተቀመጠውን አቅጣጫ ያጠናከረ ንግግራቸውን ሰምቻለሁ፡፡ በዋናነት ራስን ማጽዳት በሌላ አነጋገር ኪራይ ሰብሳቢነትን ከውስጥ መታገል ትልቁ ቁም ነገር ሆኗል፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሉት የተለዬ ነገር የለም፡፡ በእኔ እምነት ኪራይ ሰብሳቢነት እና የሙስና ችግሮች ዛሬ የተከሰቱ አይደሉም ወይም ደግሞ ኦሮሚያ እና እንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ግጭቶች ሲነሱ የመጡ ሃሳቦችም አይደሉም፡፡ ጠቅላይ ሚነስትሩ ያሉትን በትክክል ለመረዳት ከዚህ በፊት መንግስት በስርዓቱ ውስጥ አሉ ያለላቸውን ችግሮች እና ችግሮቹ ሊፈቱ ይገባል ብለው ያስቀመጧቸውን አቅጣጫዎች ወደ ኋላ መለስ ብሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡
ከዚህ ውጭ ግን ጉዳዬን ከሰሞኑ ከተነሳው ብጥብጥ እና ሁከት ጋር ብቻ አያይዞ ለሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ሃላፊነቱን የምወስደው እኔ ነኝ ያሉ ያህል አንጋዶ ለብቻው ማቅረቡ ተገቢ አይደለም፡፡
እንደ ሃገር ተጠንቶ መፍትሄው እና ችግሩ ተለይቶ የቀረበው እና እርምጃ መውሰድ የተጀመረበት ኪራይ ሰብሳቢነት በየትኛውም የሃገሪቱ አቅጣጫ ህዝቡ ላይ ችግር መፍጠሩ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ማለት ህዝቡ ጥያቄውን በስራ ማቆም አድማ፣ በሰላማዊ ሰልፍ በገለጸባቸውም ባልገለጸባቸውም አካባቢዎች ማለት ነው፡፡
ታዲያ ህዝቡ በያካባቢው በዝምታ ውስጥም ሆነ እየጠየቀ ባለበት ሁኔታ የመልካም አስተዳደር እና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች ውስጥ  እንደነበር ግን መንግስትም በጥናቱ አስቀድሞ መልሷል፡፡
ከዚህ አንጻር ኪራይ ሰብሳቢነት ምንጩ ሻእቢያ አሊያም ጽንፈኛ ቡድኖች ወይም በውጭ የሚኖሩ እና ሃገር ውስጥ ያሉ የጥፋት ሃይሎች ሊሆኑ አይችሉም፤ አይደሉምም፡፡
የዚህ ችግር ዋነኛ አቀንቃኞች ራሳቸው በስርዓቱ ውስጥ ያሉ አመራሮች ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር አባላቱም እዚህ ውስጥ ገብተው በጥቅሉ የችግሩ አካል አይደሉም፡፡ በዋናነት ችግሩ ያለው ከቀበሌ አመራር ጀምሮ እስከ ስራ አስፈጻሚ ባሉት አንዳንድ አመራሮች ውስጥ ሆኖ ይህም ሁሉንም አመራር የሚያጠቃልል አይደለም፡፡
እንዲህ ከሆነ ታዲያ የአመራሩ ባጠቃላይም የአባላቱና እና የድርጅቱ ችግር የሚሆነው እነዚህን ጠይቂት ግን ደግሞ ችግር ያለባቸውን አመራሮች መታገል እና ማስተካከል አለመቻል ነው፡፡ ስድስት ሚሊዬን ገደማ አባል ያለው ሃገር የሚመራ ድርጅት ውስጥ በሽ |የሚቆጠሩ ዝቅተኛ መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች በሚፈጥሯቸው ችግሮች እንደሃገር ህዝቡ ላይ ሸክም እንዲበዛ ሆኗል፡፡
ጉዳዬን ነጣጥለን እንመልከተው፡፡ በእኔ እምነት ጠቅላይ ምንስትሩ ወደ ውስጣችን አይተን ችግሩን በዘላቂነት እንፍታ፤ ጣታችን ወደ ራሳችን ይመልከት ሲሉ፡፡ እነዚህን ከውስጥ የተሰገሰጉ የስርዓቱን ችግሮች ራሳችን እናስወግዳቸው ለማለት እደሆነ ግልጽ ነው፡፡
በየትኛውም አካባቢ ረብሻ ከመነሳቱ አስቀድሞም ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ይህንን ብለው እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ በእኔ እይታ ትላንጽ ለርላማ የተናገሩት ባለፈው ካሉት የተለዬ አይደለም፡፡ የተለዬ የሚያደርገው ብቸኛው ነገር ያኔ እንደመነሻ እጅ ሊቆርጡ ሲነሱ ያሉት ሲሆን አሁን ደግሞ ኪራይ ሰብሳቢው ራሱን ለማዳን ችግር በመፍጠር እና ችግሮች ሲፈጠሩም ለመፍታት ባለመንቀሳቀስ እልፎ አልፎ ረብሻ ከተፈጠረ በኋላ ያሉት በመሆኑ ነው፡፡
ይህ ማለት ግን ረብሻው እንዲፈጠር ኢህደአዴግ ድንጋይ አቀብሏል ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡
ቀደም ብየም እንዳልሁት የህዝብ ቅሬታዎችን ወደ ነውጥ ሰልፍ እንዲያመሩ በማድረግ በውጭም በውስጥም ያሉት ሃይሎች ተንቀሳስዋል፡፡
ቅሬታውን ባደባባይ ለማቅረብ የወጣውን ሰው ድንጋይ እንዲወረውር እና ንብረት እንዲያቃጥል፣ ሰው እንዲገድል ግን ህዝቡም ፍላጎት ኖሮት አያውቅም፣ መንግስትም ክብሪትና ጥይት አላቀረበም፡፡ እንደሚገባኝ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩም ለዚህ የወሰዱት ሃላፊነት የለም፡፡ ይህ ማንጋደድ ነው፡፡
በጠቅላይ ምንስትሩ ንግግር በግልጽ የተባለው ግን ለችግሮች ምንጭ የሆነው እኛ ነን፡፡ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ጥቅመኝነት፣ ግለኝነት፣ እና ያላግባብ ስለጣጥንን መጠቀም ናቸው፡፡ በውስጣችን የበሰበሰው የአመራር አካል የፈጠረውን ችግር ማጽዳት ካልቻልን ችግሩ ይሰፋል፡፡ ይህ የችግሩ ስፋት እንዳይለጠጥ እና ህዝብ የሰጠንን ሃላፊነት ለመወጣት ወደራሳችን እንመልከት የሚል ግልጽ ንግግር ነው፡፡
እንደ ድርጅት እና ሃገር እንደሚመራ ሰው ችግሩን ከምንጩ መለየት እና መፍታት አለባቸውና በዚህ ንግግራቸው እኔ እንደ አንድ ኢትዬጵያዊ እኮራለሁ፡፡ በውስጣቸው ያለውን ካጸዱት እና የበሰበሰው ከተጠረገ እናንት ጽንፈኞቹ እንዴትና በየት አልፋችሁ ህዝቡ ላይ ትደርሳላችሁ፡፡ በውስጥ ያሉት አመራር ተብዬ አጋሮቻችሁ ከተቆረጡ የሚስጥር ስብሰባዎች ሳይጠናቀቁ ድምጽ ቀድቶ ማን ይሰጣችኋል፡፡ ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሉት ግልጽ ነው መሳሪያ አስታጥቃችሁ ክብሪት ሰጥታችሁ አንድዱ ላላችሁት እና ላቃጠላችሁት ሃላፊነቱ ዛሬም ነገም የናንተው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ከዚው ውጭ ግን ለዚህ መሰሉ ድርጊት ተባባሪ ለማፍራት ያስቻላችሁን እና ችግሩንም ፈጥኖ ላለማስቆም ግን አመራሩ ውስጥ ያለው ችግር አጋዥ ነበርና ይህንን ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ እጠርጋለሁ ያሉት፡፡
ይንንም እንደጀመሩት በቅርቡ በተለያዬ አካባቢዎች አይተነዋል፡፡ እንግዲህ የነ ቪኦኤ ማንጋደድ እና የጭፍራዎቻቸው ይቅርታ ጠያቂ መሪ አገኘየን ማለት ችግሩን ይህን የጠረጋ ሂደት ለማኮላሸት የታቀደ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩንም እንላቸዋለን፡፡ እዚህም እዚያም ህዝብ ላይ የጠጣበቁትን ለመጠራረግ ምንም እንደማያግድዎት አሳይተውናል፡፡ የድርጅቱ የቆየ ባህል እና ጥንካሬ ከዴሞክራሲያዊነቱ ጋር ተዳምሮ ለዚህ እንደሚያግዝዎት እናምናለን፡፡
በርቱ ክቡር ጠቅላይ ምነስትር እንልዎታለን፡፡ ሰይጣን ባለበት ጸበል ሲረጭ እንደሚንጫጫ፡፡ ይህ የሰሞኑ ጫጫታ የማጽዳት ዘመቻዎን ለማደናወፍ ነውና በያለንበት ለውጡ እንዲቀጥል እንደግፋለን፡፡
የተደናገራችሁ ካላችሁም ከሰሙ በፊት ወርቁን እዬ ምክራችን ነው፡፡

03161057
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
2977
4118
86570
75600
3161057

Since April 1, 2014

Photo Gallery