Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESየጥላቻ “ጦር ስበቁ” ለወገን መላክ ቢበቃችሁስ?

የጥላቻ “ጦር ስበቁ” ለወገን መላክ ቢበቃችሁስ?

Published in Articles
Rate this item
(0 votes)

ከሁሉ በፊት እስቲ አንድ ጥያቄ እናንሳ ምን ያህል አስበን ምን ያህል እንውላለን ማለት ምን ያህል ስለሃገር እያነሳን ምንስ ያህል ለሀገር እንሆናለን፡፡ ነው ወይስ የዳር ተመልካች ሁነን ስንጠፋም ስንለማም ከንፈር መምጠጥ እና እንደአንዳንዶቹ ማሽሟጠጥ ነው ምርጫችን፡፡ መቼም በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ዳር ሁኖ መመልከት ተመልካቹንም የምንመለከታት ሃገርንም የሚጠቅም አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ዘመኑ በንቃት የምንሳተፍበት እና ተሳትፈንም ጠቅመን የምንጠቅምበት መሆኑ አያጠያይቅምና ነው እንዲህ ማለቴ፡፡
ከዚህ አንጻር በተለይ ዲያስፖራው ያለው የመልማት እና የማልማት አቅም ከፍተኛ እንደሆነ የራሳችንንም ሆነ የሌሎች ሃገራን ተሞክሮ በማየት መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ ጽሁፌ ዋናው ርእሰ ጉዳዮም ይኸው ነው፣ ኢትዪጵያውያን ዴያስፖራዎች ለሃገራችን ያለን ድርሻ ከሌሎች ሃገራት አይን ሲቃኝ ምን ይመስላል የሚል፡፡ ጉዳዩን ከኛም ከሌሎቹም ማጣቀሻ እያነሳን እናያለን፡፡
በተለይም በበርካታ ትሪሊዮን ዶላር የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ለየሃገሮቻቸው ሲልኩ “ጦር ስበቁ” ብለው ጥላቻ ለሚልኩት አክራሪ ዲያስፖራዎች ማሳያ እንዲሆናቸው በማሰብ ይህንን ጽሁፍ አሰናድቼዋለሁ፡፡
አስቀድሜ ግን ከዶላር ይልቅ የጥፋት ወሬ ወደ ሃገራቸው ለሚልኩት የፌስቡክ እና የዩቲዩብ ተፋላሚዎች በዙሪያቸው ያሉትን ቻይናወቹን፣ ህንዶቹን እና ፖኪስታኖችን እንዲያዬ፤ አይተውም እንዲማሩ እመክራቸዋለሁ፡፡
አንባቢ ሆይ! ማንም ኢትዮጵያዊ እንደሚረዳው እኛ ብዙ ነን፡፡ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ብዙ ነን፡፡ ችግሩ እንደ ብዛታችን ለአንድ አላማ አንድ ላይ አለመሰባሰባችን እና የተቀናጀ ድጋፍ አለማድረጋችን ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ደግሞ በብዛታችንን ለልማት ሳይሆን ለጥፋት የሚጠቀሙ ጥቅም አሳዳጆች መብዛታቸው ደግሞ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያንን የጠነከረ ክንድ እንዳይኖረን አድርጎን ቆይቷል፡፡
ያም ሆኖ ለአመታት ያጠራቀመውን ቋጥሮ ሃገሩ ላይ ኢንቨስት የሚያደርገው እና ለወገኖቹ የስራ እድል ለሃገሩም እድገት እና ለራሱም እየተጠቀመ ያለ ዴያስፖራ ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ከቁጥራችን እና ከአቅማችን አንጻር የሚፈለገውን ያህል አድርገናል ወይ የሚለው ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ መረጃ ሳገላብጥ ያገኘሁት መረጃ ግን ኢትዮጵያውያን ዴያስፖራዎች ገና ብዙ ብዙ እንደሚቀረን ነው ያመላክታል፡፡
በተለየዮ ምክንያት ከሃገራቸው የወጡ ዴያስፖራዎች ቁጥራቸው ከ200 ሚሊዮን ይልቃል፡፡ ኸረ እንዴውም ይህ መረጃ አንድ ሁለት ዓመት ሁኖታል፡፡ይህ ቁጥር በየዓመቱ ወደ 3 በመቶ የሚጠጋ እድገት ያሳየል፡፡ ለአብነት ብንጠቅስ እንኳን ዴያስፖራዎቻቸው የሃገራቸው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እድገት ምንጭ የሆኑት የደቡብ ኤስያ ሃገራት በ2011 ቁጥራቸው 50 ሚሊዮን ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ይህ ቁጥር በየዓመቱ በ10 ሚሊዮን አድጎ 70 ሚሊዮን ደርሷል፡፡
ቁም ነገሩ ከየ ሃገራቸው የሚወጡ ዜጎች ቁጥር መበራከቱ አይደለም፡፡ እንዲያውም ከየሃገራቸው ከሚወጡ የተማሩ ሰዎች ሃገራቱ ሊጠቀሙ የሚችሉትን ጥቅም ያስቀራል፡፡ ያም ሆኖ በምላሹ ዜጎቹ ወደ ሃገራቸው በሚያፈሱት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሃገራቸውን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያሳድጉ ይታያሉ፡፡
እዚህ ላይ የፖኪስታንን ምሳሌ ላንሳላችሁ፡፡ የአለም ባንክ ምክትል ፕሬዘዳንት የነበሩት ሻሂድ ቡርኪ እንደጻፉት በ2013-2014 በጀት ዓመት በሩብ አመት ውስጥ ብቻ 14 ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ፓኪስታናዊያን ዲያስፖራዎች ወደ ሃገራቸው ገንዘብ ፈሰስ አድርገዋል፡፡
በአለም 2ኛዋ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት ቻይና 50 ሚሊዮን የሚሆን ዳያስፖራ አላት፡፡ ከቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ 70% የዳያስፖራው ድርሻ ነው፡፡ ህንድ 20 ሚሊዮን የሚሆን ዳያስፖራ ያላት ሲሆን ከቻይና ቀጥላ ዳያስፖራዋን በሰፊው ለልማት የተጠቀመች ሀገር ናት፡፡
የአብዛኞቹ ሀገራት ዲያስፖራዎች በቀጥታ በኢኮኖው ውስጥ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በሻገር የሃገራቸውን ምርት በማስተዋወቅ እና የሃገራቸውን መልካም ባህል ልምድና ቋንቋ በማስተወወቅ አምባሳደሮች ናቸው፡፡
መቼስ ይህ መረጃ ለሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራ ቁጭት የሚፈጠር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለፉት ጊዜያትም የድርሻቸውን የሚያበረክቱ ኢትዮጵያውያን ዴያስፖራዎቸ ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በርካቶች ራሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎችንም ወደ ሀገራቸው በመጋበዝ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ ይህን እንዘርዝር ካልን ብዙ ነውና ጊዜ ማባከን እንዳይሆን እዚሁ ላይ እናቆየው፡፡
ከዚህ በተቃራኒው ግን የሀገራቸው አምባሳደር ሊሆኑ አይደለም የሀገራቸው ጠላቶች የሆኑት አክራሪ ዲያስፖራዎች ለአባይ ግድብ ቦንድ እንዳይሸጥ እየተቃወሙ ለአሸባሪው የኢሳት ቴሌቪዥን ገንዘብ ሲያዋጡ ነው የሚስስተዋለው፡፡ ኢትዮጵያያን የዘመናት የመልማት ጥያቄያቸውን አባይ ላይ ታሪክ በመጻፍ ሲተጉ የኢሳያስ ድንቢጦች ግን ይህንን እየተከላከሉ የውሸት አጋፋሪያቸውን እና እንጀራቸው ኢሳትን ያበስላሉ፡፡
እንዳንዶች ኢሳትና ዬቲዬብን በመጠቀም የተፈጠሩ ጀግኖችን በማወደስ ተጠምደው ሃገር ይሉትን ጥልቅ ነገር ህዝብ ይባል ጽኑ ፍቅር ወገን ይሉት ሰፊ ሃቅ ትተው ከሻእቢያና ግንቦት 7 ጋር ፍቅር ወድቀዋል፡፡
በግንቦት 7 አፍ ቴሌቪዥነ የሚቀርበውን ፉገራ ተከትለው የሚባዝኒ ኢትዮጵያዊያንም አሉ፡፡
ያም ሆነ ይህ እነዚህ የግንቦት 7 ጥገት ላሞች በባዶ አፍ ቤተሰቦቻቸውን በጥላቻ ወሬ ከሚያደንቁሩ ጠብ የሚል ነገር ቢያደርጉ ለራሳቸውም ለሃገራቸውም ጥቅሙ የላቀ ነውና ሊያስቡበት ይገባል እንላለን፡፡
ውድ አንባቢዎቼ ይህን የምላችሁ የነቻይናን የህንድን እና የሌሎችንም ሃገራት ተሞክሮ በማየት ብቻ አይደለም እዚህ ያሉት አክራሪ ዲያስፖራዎች በከንቱ የጥላቻ ወሬያቸው ቤተሰቦቻቸወንም እያሰለቿቸው ነው፡፡ ይህንን ስል ለብዙዎቻችሁ ላይገባችሁ ይችላል የደረሰባቸው ግን ያውቁታል፡፡
አንዳንዶቹ የኢሳትን የፈጠራ ወሬ ሰምተው “አማራውና ትግሬው እርስ በእርሱ እንዲህ እየሆነ ነው! እንዲያ እየተደረገ ነው! ይባላል እንዴት ነው” ይላል አክራሪ ዲያስፖራው ከውጭ፡፡
“እረ ወንድም ጋሼ የምታወራው ምንድን ነው ሁሉም ሰላም ነው” ይመልሳል ከሃገር ቤት፡፡
መደማመጥ ይጠፋና ስልኩ በልዬነት ይዘጋል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ስልክ ይደወላል፣
“ስማ እንጅ ሙስሊሙና ከርስቲያኑ ተቃቅሯል ክፍኛ እልቂት መምጣቱ አይቀርም እየተባለ ነው፡፡ ደግሞ የብሄር ልዮነቱም ከፍቷል በጣም መከፈፋፈል አለ እየተባለ ነው፡፡ እባካችሁን ተጠንቀቁ፡፡ እናታችንንም አደራ” ይለል አክራሪ ዲያስፖራው፡፡
“እንዴ ወንድም ጋሼ ምንድን ነው የምታወራው! እኛ በሰላም በፍቅር እየኖርን ነው፡፡ ምንም ተለወጠ ነገር የለም” ይላል ታናሽ ከሃገር ቤት፡፡ ይህኔ ታላቅ ይቆጣል፡፡ ወንድሙን መርዳት ሲገባው በስልክ ሊያስተላልፍ የፈለገው የጥላቻ ወሬ ከንቱ ይሆናል፡፡ በሀገርቤት ካለው ተጨባጭ ሁቤታ ጋር ያነሳው ሃሳብ አልጣጣም ይላል፡፡ እውነት ከውሸት ጋር ተገጣጥሞ አያውቅምና ውሸቱን እውነት ለማድረግ የሚለፋው ታላቅ ታላቅነቱ በጥላቻ ወሬው የይቀላል፡፡
ከመንድሙ ጋር ይጣላል፡፡ እና ሌላ ጊዜ ሲደውል ለታናሹ የሚመታደቅበትን ፍርፋሪ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ሰላምታም ይነፍገዋል፡፡ በቁጣ “እማየ ያንን ልጅ ላገኜው አልፈልግም፡፡ ዋና ወያኔ ሁኖ የለ እንዴ!!” ሲል ድሃ እናቱ ላይ ይደነፋል፡፡
በቃ ይኸው ነው የነንቦት 7 አላማ ወንድምን ከወንድም ማለያየት፡፡ ህዝብን እንደ ህዝብ ማቃረን! እውነት ሚናገርን ሃገር እና ህዝብ የሚልን ልማት ልማት የሚልን መፈረጅ ብቻ!!
በነገራችን ላይ ከላይ ያነሳሁላችሁ የወንድማማቾቹ ምሳሌ ነገሬን ለማሳመር ያነሳሁት እንዳይመስላችሁ እወነተኛ ታሪክ ነው፡፡ ወደ ፊት ሰፋ አደርጌ እመለስበታለሁ፡፡
ሃሳቤን ላጠቃል “ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ጆሮ ያለው ይስማ!!” ያለው ማን ነበር….ብቻ ማንም ይሁን በታሪካዊ ወቅት ታሪክና አጋጣሚ ፈጥሮልን ሃገር በምታድግበት የዘመን ምእራፍ ላይ የቆምን ኢትዮጵያውያን እውነቱን ልብ እያልንና እየሰማን የእድገት ጉዟችንን ልናፋጥን ይገባል ባይ ነኝ፡፡ በተለይ ዲያስፖራው ለዚህ ትልቅ አቅምም ያለው፣ ሀላፊነትም ያለበት ነውና ለዚህ ሊተጋ ይገባል፡፡ እንዳለመታደል ሁኖ አክራሪ ዲያስፖራዎች ግን ሃገራቸውን ከማልማት ይልቅ ሃገራቸውን ማድማት የሚመርጡ ናቸው፡፡ በሃገራቸው ልማት ተሳትፈው የተጣመመውን ከማቃናት ይልቅ የራሳቸውን የሻእቢያ አቃጣሪ ጀግኖች ፈጥረው የሚያቅረራሩ ናቸው፡፡
ከላይ ያነሳሁት ሃሳብ ሃገር ወዳድ ዲያስፖራዎችን የሚመለከት አይደለም፡፡ በመግቢያዬ ላይ እንዳነሳሁት እነሱ የድርሻቸውን ጠጠር እየጣሉ ነው፡፡ ብዙ ነን፡፡ እንደብዛታችን የበዛ ያቅማችንን ጠጠር ብንጥል አባይን አይደለም ሃገርን በልማት እንሞላለን!!!

03040965
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1049
1650
42078
51980
3040965

Since April 1, 2014

Photo Gallery