You are here: HomeARTICLESዴሞክራሲ የብዙሃን ተሳትፎ የሚያፈካው ነው ካልን የጥቂቶች ጫጫታ እንዲያቀጭጨው ለምን እንፈቅዳለን? ከጽናት ራዲዬ፣ በሰለሞን ተካልኝ

ዴሞክራሲ የብዙሃን ተሳትፎ የሚያፈካው ነው ካልን የጥቂቶች ጫጫታ እንዲያቀጭጨው ለምን እንፈቅዳለን? ከጽናት ራዲዬ፣ በሰለሞን ተካልኝ

Published in Articles
Rate this item
(1 Vote)

ዴሞክራሲ ዴሞ እና ክራቶስ ከተባሉት ሁለት ቃላት ተመስርቶ ጥቅል ትርጉሙ የህዝብ አስተዳደር የሚለውን ይያዝ እንጅ በሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ከዚህ ጥሬ ትርጉሙም ባሻገር ከታሪካችን ጋርም ተናቦ እድገቱም፣ ውድቀቱም መታየት አለበት፡፡
በዚህ ረገድ ልማትና ዴሞክራሲን የማስቀጠል ጉዳይ በዚህ ስርዓት ድህነት ጠላታችን ነው ብሎ በማመን የጀመረ፣ ልማት ከናዳ እንደማምለጥ እድገትን በፍጥነት የማስቀጠል የህልውና ጉዳይ እንደሆነ ታምኖበት መገባቱ የሚታየውን ለውጥ አምጥቷል፡፡
በሂደቱም ሃገርን ማሳደግ፣ የህዝቦችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንደተቻለ በበርካታ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡
የዴሞክራሲ ስርዓት ግባታ ጉዳይም ሃገሪቱ ከቆየችበት ረዥም የጸረ ዴሞክራሲ ስርዓት ጋር  ሲነጻጸር ጊዜ እንደሚፈጅ የሚታመንበት ጉዳይ ቢሆንም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ተግባራዊ በማድረግ የመድብለ ፖርቲ ስርዓትን በማጠናከር ይበል የሚያስብል ሂደት ውስጥ እንዳለን መናገር ይቻላል፡፡
ይህም ሆኖ በዴሞክራሲ ስርዓታችን ውስጥ የሚከሰቱ ደንቃራዎችን ለማረም የሚደረገው ሂደት ከዴሞክራሲ ተቋማቱ ልምድና ጥንካሬ እንዲሁም ጅምር ላይ ካለው እድገታችን ጋር ተያይዞ ፈተናዎች የበዙበት እንደሆነ ቢታይም አሁንም ግን ሂደቱ የመስመሩን ጥንካሬ እንደሚያሳይ የሚስማሙት ብዙዎች ናቸው፡፡
እንደ ተግዳሮት የሚነሳው ግን ለዴሞክራሲ ስርዓታችን ደንቃራዎችን የምናርምበት ሂደት ቀርፋፋ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሂደቱ አንዳንዴ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከፕሬስ ነጻነት ጋር እየተጣበቀ ቻይና ታጋሽ፣ ይቅር ባይና ተናካሽ የሚሆንበትን ነገር የዴሞክራሲን ጉዳይ በሰውኛ ባህሪ የማጀል አስተያየት ያለው ነው፡፡
ለምንድን ነው ይህን የምለው የዴሞክራሲ ጉዳይ ሰውኛ ነገር አይደለም፡፡ ቸር፣ ደግ የሚሆን ይቅር ባይ ክፉ የሚሆን አይደለም፤ ምክንያቱም ዴሞክራሲ ስርዓት ነው፡፡ ስርዓት ደግሞ በህዝቦች ብዙ መስዋእትነት የሚገኝ እና የሚመጣ፣ ከአለም አቀፍ መርሆች ጋር የሚጣጣም እንጅ ማንም እንደፈቀደው የሚያደርገው የችሮታ ጉዳይ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ምናልባትም እንደ ሃገር በሁሉም ተቋማት እንደሚታየው ሁሉ የፍትህ ስርዓታችንንም ማየት ተገቢ ነው፡፡ በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚታየው መጓተት ሂደቱን ከማልካም አስተዳደር ችግርነት ባለፈ ስርዓታችንን ጥርስ የሌለው ውሻ እንዳያስመስለው መጠንቀቅም ያስፈልጋል፡፡
ዴሞክራሲ የህዝቦች ነው ስንል የብዙሃን ድምጽ የሚያፈካው እንጅ የጥቂቶች ጫጫታ የሚያፈርሰው አይደለም ማለት ነው፡፡ እርግጥ ነው በጥቂቶች ጫጫታ አሁንም ይፈርሳል ብዬ አላምንም፡፡ ከሰሞኑ የሃገራችን ሁኔታ አንጻር መነሳት ያለበት ነጥብ ግን ዴሞክራሲ የብዙሃን ተሳትፎ የሚያፈካው ነው ካልን የጥቂቶች ጫጫታ እንዲያቀጭጨው ለምን እንፈቅዳለን? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡
20 ሺህ ህዝብ ባለበት ከተማ 20 ሰዎች ተቋም ሲያቃጥሉ የህዝቡ የሚመስለን ለምንድን ነው? ከ20 ሰዎች ውስጥስ ስንቶቹ ናቸው በጥላቻ የተሰለፉት? ሁሉንም በጥላቻ እና በወዳጅነት ፈርጆ መሄድ የአንድ የፖለቲካ ስርዓት ባህሪ ነው ወይ? አይደለም፡፡
እዚህ ላይ ምናልባትም ከ20ዎቹ ሰዎች ውስጥ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ባሉት የመዋቅሩ ችግሮች የተነሳ ቅሬታ ያለባቸውም ይኖራሉ፡፡
ምናልባትም ምናልባትም ከ20ዎቹ 18ቱ ወይ ስራ ባለማግኘታቸው አሊያም በጠባብ ወይ በትምክህተኛ አለቆቻቸው ስራ የለቀቁ አሊያም በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ሃገሩ ያስጠላቸው ይሆናሉ፡፡
ምናልባትም የነዚህ ሰዎች መሰረታዊ አላማ ቢጣራ መቃዎም እንጅ መግደል ማቃጠል አይሆንም ይሆናል፡፡
ግን ደግሞ ከ20ዎቹ ውስጥ ሁለቱ ጽንፈኛ አሊያም አክራሪ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ቅሬታዎችን በማሰባሰብ አቅም ፈጥረው መዋቅሩን ለመናድ የሚሹ የጥፋት ሃይሎችም ናቸው፡፡ እነዚህ የመግደል፣ የማፍረስ፣ ተቋማትን የማቃጠል አላማ ያላቸው ናቸው፡፡ ግን ደግሞ የ18ቱን ቅሬታ ወደ ጥፋት የመምራት አቅም ያላቸው ይሆናሉ፡፡
በኔ እምነት አሁን በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ነገር መነሻውም መድረሻውም የተደበላለቁ ፍላጎቶችና ውጤቶች ናቸው፡፡
መንግስትም በግልጽ እንዳስቀመጠው ቀደም ብሎ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በተነሳው ግርግር ውስጥ የህዝብ ጥያቄዎች በበሩበት፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በመንግስት በኩል ተገቢውን ምላሽ የተሰጠባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን አልፎ አልፎ አጠቃላይ ሃገሪቱ ላይ እንደሚታየው እዚህም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ከአፈጻጸም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ህዝብን ቅሬታ ውስጥ የሚከቱ ጉዳዬች ይነሳሉ፡፡
ዋናውን ሃሳቤን ይበልጥ ላብራራው፡፡

·    የመልካም አስተዳደር ችግር
·    አመራሩ ቸልተኝነት፣ ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን እንዴት እንፍታው
·    የስራ አጥነት እና መሰል ጉዳዬች የትም ይኖራሉ፡፡
እነዚህ በየትኛውም ክልል በእድገት ውስጥም ሆኖ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች ባሉበት የህብን ቅሬታዎች ወደራሳቸው ፍላጎት ለመቀልበስ የሚፈልጉ ሃይሎችም አሉ፡፡ እነዚህ የነጃዋር ተላላኪዎች ገጠር ድረስ ወርደው ለመስራት ተንቀሳቅሰዋል፡፡
በዚህ ሂደት ግን የክልሉም ሆነ የፌዴራል መንግስት ጥቂት ሆነው ግን ደግሞ ግርግር ለማስነሳት አቅም ያገኙትን ሃይሎች ቀድሞ ለመከላከል ያልቻለው ለምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ነው፡፡
አስቀድሞ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ የጋራ ማስተር ፕላን ላይ መሰረት አድርጎ የተነሳው ብጥብጥ ከተቋጨ በኋላ ዛሬ ደግሞ ባዲስ መልኩ በምእራብ አሩሲ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከቀደመው በከፋ የጥፋት ደረጃ ብጥብጦች ተነስተዋል፡፡
ይህ አይነቱ የጥፋት እንቅስቃሴ ከህዝብ ጥያቄ ጋር እንደማይገናኝ መንግስት አጽንኦት ሰጥቶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
እንዲህ ከሆ ጥያቄው የጸረ ህዝብ አቋም አራማጆች ናቸው ማለት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ጸረ ህዝብ ማለት ደግሞ ሽብርተኛ ጽንፈኛ እና አመጸኛና ወንጀለኛ ነው ማለት ነው፡፡
በእርግጥም ወንጀለኛ አመጸኛ እና ሽብርተኛ መሆናቸውን ያሳዬበት የቃጠሎ እና የሽብር ተግባራትን ፈጽመው በኢቢሲም አይተነዋል፡፡
መንግስትም በጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም እና በቃል አቀባዬ አቶ ጌታቸው ረዳ አማካኝነት እንዳስጠነቀቀው አሁን ላይ የመንግስት ዋነኛ ተግባር የህዝቡን ደህንነት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጠበቅ ነው፡፡
በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ግን የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል፡፡
ይህ መሆኑ ጥሩ ነው፡፡ እንደ ጽናት ራዲዬም የምናደንቀው እና በርቱ ቀጥሉበት ዴሞክራሲን የመጠበቅ ጉዳይ በሰውኛ ባህሪ በችሮታና በታጋሽነት የሚፈታ ሳይሆን እንደ ስርዓት በመዋቅሩ የህግ የበላይነት መፈታት አለበት እንላለን፡፡
ምክንያቱም ህግ ጥርስ ሲኖረው፣ ያጠፋን መንከስ ሲጀምር ያኔ ሰላምንም የህግ የባላይነትንም ማስከበር ይቻላል፡፡ ከዚህ አንጻር እስካሁን በህዝቡ ጥረት ጥፋተኞችን ማስቆም ተችሏል የሚለው ዘገባ እና ሪፖርት ተቀይሮ መንግስት በጥፋተኞች ላይ ይህን እርምጃ ወሰደ የሚለውን እንድናይ እንድንሰማ እንናፍቃለን፡፡
እርግጥ ነው ለዚህ መነሻ እና መንደርደሪያ የጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ማስጠንቀቂያ ብቻውን በቂ ይመስለኛል፡፡
ይህ ብእንዲህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እ የተመኘየን  ያለፈውን እና ያለውን ስናይ ደግሞ ዘላቂ መፍትሄው ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
የውነቴን ነው፡፡ የዚህ የኦሮሚያ ጉዳይ ነዶ ሲበርድ አሁን ለሶስት አራተኛ ጊዜው መሀኑ መሰለኝ፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ እሳት ሲነሳ በማጥፋት ብቻ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ይቻላል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፡፡
እርግጥ ነው እሳት ሲነሳ ማጥፋት ሃላፊነት የሚሰማው ሰው ድርሻ ነው፡፡ ግን ደግሞ እሳት ሲነሳ ሁሌ ከማጥፋት እሳቱ እንዳይነሳ በዘላቂነት መፍታት ትልቁ መፍትሄ ይመስለኛል፡፡
ለዚህም ነው ከላይ በመግቢያዬ እንዳነሳሁት ህዝብ ቅሬታ ምንጭ የሆኑትን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና መሰል ችግሮች ያለ ምህረት በትግል መፍታት ያስፈልጋል ያልሁት፡፡

03161058
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
2978
4118
86571
75600
3161058

Since April 1, 2014

Photo Gallery