Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESእንቁራሪቷ ተቀቅላ እክስትበስል ሞቷን አታውቀውም፣ ዓለሙም ከድስቱ አፍ የሰፋ ነው - ከጽናት ራዲዬ በሰለሞን ተካልኝ

እንቁራሪቷ ተቀቅላ እክስትበስል ሞቷን አታውቀውም፣ ዓለሙም ከድስቱ አፍ የሰፋ ነው - ከጽናት ራዲዬ በሰለሞን ተካልኝ

Published in Articles
Rate this item
(2 votes)

ለዛሬ በሃገር ቤት ወግ ጽሁፌ የማወራላችሁ ሞቷን ስለማታውቀው እንቁራሪት ነው፡፡ የእንቁራሪቷን ባህሪ ከውስጥም ከውጭም የሚመስሉ ብዙ እንዳሉ አስረግጨ መናገር እችላለሁ፡፡ ከእንቁራሪቷ ባህሪ ውስጥ ከየትኛው ውስጥ መሆንን ለራስ መጠየቅ ነው እንግዲህ፡፡
የሻእቢያ የመስመር አራጋቢዎችን ግን አስቀድመን “እኛ ስራ ላይ ነን” ብቻ ሳይሆን “እድሉን ብታገኙት እንደ እንቁራሪቷ ትዘሉ ነበር” እንላቸዋለን፡፡
ወጋችንን እንቀጥል፡፡
ይህ እውነተኛ የእንቁራሪት ባህሪ ነው፡፡ እንቁራሪትን በብረት ድስት ውስጥ ባለ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ጨምረው እሳት ላይ ከነብረት ድስቱ ቢጥዷት፣ በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ሆና እሳት ላይ በመጣዷ ብቻ አትዘልም፡፡ ውሃው ቀስ በቀስ እየሞቀ… እየሞቀ…እየሞቀ ሄዶ መፍላቷን፣ መቀቀሏን ሳታውቀው ትሞታለች፡፡ ምክንያቱም ቀድሞ የገባችበት ምቹው የውሃ ቅዝቃዜ እንጅ በሂደት የፈላው ውሃ ነፍሷን እስኪነጥቀው ድረስ አታውቀውም፡፡
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ያችኑ እንቁራሪት ፈልቶ በሚንተከተክ ውሃ ላይ ቢጨምሯት ዘላ...ተስፈጥራ ትወጣለች፡፡
የአንዳንዶቹ ሰዎችም ባህሪ ይህ ነው፡፡ በተለያዬ መልኩ ይህን ሲመስሉ እናያቸዋለን፡፡ እርግጥ ነው ይህ የእንቁራሪቷን ባህሪ መምሰሉ በእውቀትም ያለ እውቀትም ሊሆን ይችላል፡፡ በሃገር ጉዳይ እድገት፣ ለውጥ፣ ብልጽግና እያልን ስናወራ የማይጥማቸውን ጽንፈኞች ተመልከቷቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች በቀዝቃዛው ውሃ ውስጥ ገብተው ጥፋት እየፈላባቸው ያሉ ሰዎች ናቸው ብል እያጋነንኩ ነው ብዬ አላምንም፡፡
አንዳንዶቹ ኢህአዴግ እና ህዝብ ከበርሃም ከከተማም ጠርጓቸው ከ25 ዓመት በፊት አውሮፓና አሜሪካ የከተቱት ሰዎች ያኔ ጀምሮ የገቡበት የጥላቻ ብረት ድስት በየጊዜው እየሞቀ፣ እየፈላ….እየፈላ ዛሬ ሩብ ክፍለ ዘመን ደርሷል፡፡
ይሕ የመፍላት ሂደት አንዴ ገብተውበት በየጊዜው እያደገ የሄደ ነውና ከውጭ ያለው ተመልካች እነሱ አጉል በጥላቻ እየተቀቀሉና እየሞቱም እንደሆነ እያዬ እንደእንቁራሪቷ የጥላቻቸውን ሙቀት ከነባራዊው ሁኔታ ጋር አጣጥመው መለካት ሳይችሉ ሙቀቱ ብቻም ሳይሆን እርጅናውም ወደ ሞት እየወሰዳቸው ነው፡፡
እነዚህን ሰዎች እንዴው እድሉን አያገኙትም እንጅ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ትተዋት የመጧትን ሃገር ላይ ድንገት ወስደው ቢጥሏቸው የፈላ ውሃ ውስጥ እንደገባችው እንቁራሪት ልማቱ አስደንግጧቸው በዘለሉ ነበር፡፡ ታዲያ በዘለሉ ስል አንድም በደስታ አሊያም በንዴት ሊሆን ይችላል፡፡ መዝለላቸውን ግን መጠራጠር አይገባም፡፡
እድገቱን እና የለውጡን ሙቀት ድንገት ሲያዬ በግርምት መዝለላቸው አይቀርም ነበር፡፡ ግን ይህንን ለማየት መታደል ይጠይቃል፡፡
እዚህ ሃገር ቀስ በቀስ እየፈላ ሄዶ መንተክተክ የጀመረ የጥላቻ እንቁራሪቶችን የዋጠ ድስት አለ፡፡
እዚያ ሃገር ሃገር ቤት ግን ልማት እድገት በፍጥነት የሚፍለቀለቅበት ሁኔታ በመኖሩ ነው ይህን ማለቴ፡፡
ቀስ በቀስ ጥላቻችሁ እያነፈራችሁ እርጅናውም በዚያው ልክ እየፈጃችሁ ያላችሁትን ሳስብ እንደ ሃገር ሰው እንዳንዴ ሃዘን ቢጤ ውስጤን ይሸነቁጠዋል፡፡
ከዚህ በፊት በጽናት ራዲዬ ላይ ደጋግሜ ብየዋለሁ፤ አንዳንዶቻችሁ በውጭ ያላችሁ የቀድሞ ስርዓት ባለስልጣናት ሃገሪቱ ያኔ ትታችኋት የመጣችኋት ያው ያች የተጎሳቆለች ሃገር እንደመሰለቻችሁ ማለፋችሁ በጣም ያሳስበኛል፡፡ ሃገር ቤት ባትሄዱም ስለ ሃገር ቤት የምትሰሙትን የምታዬትን እንዳታምኑ እንኳን ገና ድሮ በቀዝቃዛው ገብታችኋልና የለውጡ ሙቀት አይታያችሁም፡፡
እንቁራሪት የገባችበትን እንጅ የሚሆነውን ለማየት ባህሪዋ እንደማይፈቅድላት ሁሉ እናንተም በያዛችሁት እንደተገተራችሁ ከድስቱ ባሻገር የሚሆነውን ለማየት ባህሪያችሁ አልፈቀደም፡፡
ውድ አድማጮቼ መቼስ ይኸ የሃገር ቤት ወግ አይደል፡፡ የእንቁራሪትዋን ታሪክ ሃገር ወስጥ ባሉት ሰዎች ምሳሌ ደግሞ እንየው፡፡ ሃገር ውስጥ ባሉት ስል ተቃዋሚ፣ ደጋፊ፣ ገለልተኛ፣ ዝምተኛ፣ ጩኸተኛ፣ ድንጋይ ወርዋሪ፣ ድንጋይ ከማሪ ሁሉንም ይመለከታል፡፡ የትኛውንም ሃገር ውስጥ ያለውን ልማት እና እድገቱ ወደፊት በሄደበት እና ሃገር በተለወጠበት ልክ የማይታያቸውን ሁሉ ይመለከታል፡፡
ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ እያደገ ያለው ሃገር በያንዳንዱ እድገት ልክ እድገቱን እየተጠቀመ እዚያው በውስጡ ያለ ሰው እንዳንዴ የለውጡን መጠን በቅጡ ላይገነዘበው ይችላል፡፡
ምክንያቱም እዚያው ውስጡ ነው ያለው፡፡
ከ20 ዓመት በፊት በቀየው መንገድ ሲቆፈር፣ በመቆፋፈሩ እየተማረረ ቆይቶ በኋላም መንገዱ ሲሰራ ደስ ብሎት ሲመላለስበት ኖሮ..ኖሮ………
ደግሞ ከሌላ አመት በኋላ….ሌላ መንገድ……ደግሞ ሌላ…...መቆፈር መሰራት….መቆፈር፣ መሰራት…ያጋጥመዋል፡፡ ይህ እንግዲህ የለውጥ ሂደት ነው፡፡
ይህን ሂደት በፈተናው ውስጥ እያለፈ፣ በስኬቱ እየተጠቀመ ያለ እዚያው የሚኖር ሰው የእድገቱ ለውጥ፣ ሂደቱን ያላየውን ሰው ያህል ሊያስደንቀው አይችልም፡፡
ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በሃገር ልማት ላይ የወጣቶችን እና የአዛውንቶችን አስተያየት ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡
ከኢህአዴግ በፊት አንድ ሁለት መንግስት ያሳለፉት አዛውንቶች ላሁኑ ለውጥ በትንሹም ቢሆን ማነጻጸሪያ አላቸው፡፡ በሌላ መልኩ ወጣቶችን ስናይ ደግሞ የቀድሞውን ያዬትን ያህል አይደለም ግርምታቸው፡፡ ግን ደግሞ ለውጡን ሁሌም ያዬታል፣ ያጣጥሙታል፣ በመንገዱም ይመላለሳሉ፡፡
በሌላ በኩል ከ10እና ከ15 ዓመት በፊት ከወጣበት ከተማ ድንገት የተመለሰ ሰው በከተማው ለውጥ ተደናግጦ እንደ እንቁራሪቷ በድንጋጤም ባይሆን በግርምት ሊዘል ይችላል፡፡ ምናልባትም…ምናልባትም ያደገበት ቤት አቅጣጫው ጠፍቶት ጠቁሙኝ ባካችሁም ሊል ይችላል፡፡
ይህ እንግዲህ ሰውኛ ባህሪ ቢሆንም እዚህ ባውሮፓ እና በአሜሪካ ያሉት ጽንፈኞች ማለቴ ጆሮና አይናቸውን ደፍነው የሚሆነውንም የሚደረገውንም አንሰማም የሚሉት ግን ከድስቱ ስፋት ውጭ አለሙን ማየት የማይችሉ ናቸው፡፡ የኔ ነገር ማየት የማይችሉ አልኩ እንጅ አንዳንዶቹ የማችችሉ ብቻም ሳይሆኑ ለውጡን ማየት የማይፈልጉ ጭምር ናቸው፡፡
እንዲህ አይነቶቹን አለማችሁን ባለሙ ልክ ባይሆንም ባገራችሁ ልክ አስፉት እባካችሁ ከማለት ውጭ ለጊዜው ሌላ ምክር የለኝም፡፡ ከቀዝቃዛው ብረት ድስት ውስጥ ውጡ! ሞታችሁ የፈላ ነውና የሃገራችሁን ጉዳይ እውነቱን እዬ የምንለው ለዚህ ነው፡፡
ከአረብ ሃገር ረብጣ ተቀብለው ሞት በፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ እየለጠፉ ወጣቱን ለሞት የሚጣሩ የሙታን መንፈሶች በቀዝቃዛው ድስት ውስጥ ቀድመው ገቡ ናቸው፡፡
ሻእቢያ በኢትዬጵያዊያን ጀግኖች የተጎነጨው የሽንፈቱ ጽዋ በእጅ አዙር በጽንፈኞች እንዲወራረድለት ግንቦተኞችን ሲጠቀም ከቆዬ ይኸው ስንት ዘመን ተቆጠረ፡፡
እነዚህ የሻእቢያን ፖለቲካ የጫኑ እና፤ እነዚያ የአክራሪነትን ዘመቻ የተሸከሙ ሁለቱም የሚፈልጉት ግን እንድንፋጅ ነው፡፡ እንድንጫረስ፣ እንድንባላ፣ እንድንተላለቅ፣ ሃገር የደም ጎርፍ እንዲውጣት ነው ፍላጎታቸው፡፡
መቼም እንዲህ ያስባለህ ምንድን ነው ብላችሁ አትጠይቁኝም፡፡ በዚያ ሰሞን አዲስአበባ ዙሪያ እና ጎንደር መተማ ጭልጋ የሆነውን መቼም አታጡትም፡፡
አክራሪው፣ ትምክህተኛው፣ ጠባቡ ሁሉም ባንድ ተሰልፎ እረብሻው እንዲቀጥል፣ ሞት እንዲፋጠን ያላደረጉት ጥረት ነበር እንዴ?
አይ ሃገር! ሃገር እንደ እምቧይ ካብ የሚናድ መስሏቸው ጃዋር ከዚህ፤ መራራ ከዚያ፤ ብርሽ ከአውሮፓ፤ ይልቃል ከአፍሪቃ በቃ! አበቃ! የመጨረሻው ነው አሉ! እዬት እንግዲህ የምኞታቸውን ጥግ የት ድረስ እንዲዘልቅ እንደሚፈልጉ፡፡
በነሱ ምኞት ልክ እኮ የሩዋንዳው አይነት መጨራረስ ውስጥ ብንገባ ደስታቸው ነው፡፡ ግን ደግሞ “ሳይደግስ አይጣላም” እንዲሉ አረም ያበቀለ ሃገር ፍሬው ብዙ ነውና አረሙ ቦታ የለውም፡፡
“በቃ!” ብለው ሲያውጁ “ራሳችሁ በቃችሁ፣ እኛ ስራ ላይ ነን” ያላቸው ራሱ ህዝቡ ሆነ፡፡ ደስ ነገር ምን መሰላችሁ እነሱ ሳይጣድ ሚገነፍል ህዝብ አድርገው ይቆጥሩታል እንጅ ይህ ህዝብ ታላቅ ነው፡፡ ታላቅ ብቻ ሳይሆን አዋቂም ነው፡፡ ባለታሪክ ነውና ከሌሎች ብቻ ሳይሆን ከራሱ ታሪክም ተምሯል፡፡
እናንተ አረቦቹ በሻእቢያ በኩል ፍርፋሪ ሲጥሉላችሁ አንድ ሳምንት የምትሉት የሃገር ጉዶች ናችሁ መቼም፡፡
ህዝብና መንግስትማ ስራ ላይ ናቸው፡፡
በዚህ የሃገር ቤት ወግ በኩራት የምናወራው ይህንን ነው፡፡ እንዲያ “ወያኔ አበቃለት” በምትሉበት ሳምንት ነው የህዳሴው ግድብ ግንባታ ወሳኝ ምእራፍ እንደተጠናቀቀ የሰማነው፡፡
ሃገርና ህዝብ የታላቁን ወንዝ አቅጣጫ እንደፈለጉ መቀያየር በጀመሩበት ዘመን እናንተን ሻእቢያ እንደራዲዬ ጣቢያ መፈለጊያ እጀታ እንደፈለገ ያዟዙራችኋል፡፡
መቼም ይህ የሃገር ቤት ወግ አይደል፡፡ ከቻላችሁ በኢሳት አንድ ሰበር ዜና ለሻእቢያ ስሩ እና ነጻነታችሁን አውጁ፡፡ “ሻእቢያ ሆይ እጆችህን ከጆሯችን ላይ አንሳ” በሉት፤ “እንደፈለግህ ጆሯችንን ይዘህ አትጠምዝዘን” በሉት፡፡
ያው እንደነገርኳችሁ ሃገር እና ህዝብ ስራ ላይ ናቸው፡፡ ሁሉም ይሰራል፡፡ እርግጥ አምቡላንስ አቃጥሉ የተባሉትም እንደስራ ቆጥረውት እሱን አድርገውታል፡፡ ግን ደግሞ ህዝቡ አምቡላንሱ ለነፈሰጡሮች ነው አታቃጥሉት፣ በቃችሁ ብሏቸዋል፡፡ ምክንያም ህዝቡ ስራላ ላይ ነው፡፡ የሚያሳካው ራእይ፣ የሚደርስበት ግብ አለና አንሰማችሁም እያለ ነው፡፡
የቆምነው የህዳሴ ራእይ ለማሳካት ነው፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም፣ ሞቃችሁም በረዳችሁም ይህች ትላንት ታላቅ የነበረች ሃገር ታላቅነቷን የሚመልሰው ይህ ትውልድ ነውና የሚሮጠው ለዚያ ነው፡፡
ከዚያ ሩጫው ለማስቆም የሚሞክር ሁሉ እንደደርግ ከመንገዱ መጠረጉ አይቀርም፡፡
ፌስቡክ እና ሌሎችንም ሶሻል ሚዲያዎችን ሙዚቃ በሉት መረጃ፣ ዜና በሉት ዘነዘና ጥፋትን ለማንበብ ጊዜ የለንም ያለ ህዝብ ያለበት ሃገር ነው፡፡
ዛሬ ሃገሩ ለባላገሩ የእድገት እና የለውጥ ነው! ስራ ላይ ነን፡፡

03040956
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1040
1650
42069
51980
3040956

Since April 1, 2014

Photo Gallery