Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESየዴሞክራሲ ዋጋው ምን ያህል ሰላም ነው (ከጽናት ራዲዬ)

የዴሞክራሲ ዋጋው ምን ያህል ሰላም ነው (ከጽናት ራዲዬ)

Published in Articles
Rate this item
(0 votes)

ሁዳድ ሰፊ የእርሻ መሬት ማለት ነው፡፡ ሃገር እንደዚያ ነው - እንደ ሰፊ ለም ሁዳድ፡፡ በሰፊው ለም ሁዳድ ላይ ምርጥ ዘር እስከተዘራበት ድረስ ሰብሉ ያማረና ፍሬው ያሸተ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም ያህል ሰብል ያማረ እና የሚያስጎመጅ ቢሆንም በማስተዋል ካየነው ግን ጥቂትም ቢሆን አረም አይጠፋውም፡፡ ያም ሆኖ ከስፋቱም ከብዛቱም አንጻር ለምን ጥቂት አረም በውስጡ በቀለ ተብሎም ከሰፊው ምርጥ ሰብል ይልቅ አረሙን ማየቱም ትክክል አይደለም፡፡ ሰብሉም የሚጠራው እና የሚገለጸው በብዙው ያማረ ሰብል እንጅ በጥቂቱ አረም ሊሆን አይችልም፡፡
ይልቁንም አረሙ እንዳይሰፋ እና ማሳውን እንዳያበላሽ መነቀል አለበትና ገበሬው ለዚህ ይተጋል፡፡ ይህ የገበሬ ስራ ነው፡፡ መነሻው ደግሞ አረም ሰብል ስለሚበክል ከዋለ ካደረ የማሳውን መገለጫ ከጥሩነት ወደ መጥፎነት ስለሚያመጣ አረም ሁልጊዜም ገና በትንሽነቱ ሳይበዛ መነቀል አለበት፡፡
አረም በገበሬ ቋንቋ ጸረ ምርት ነው - ጸረ ሰላም በሉት ከፈለጋችሁ፡፡ እኛም በሰፊው ማሳ ምሳሌ ውስጥ የምንኖር ያማርን እና እያደግን ያለን የምናስቀና የአዲስ መንገድ ተጓዥ ዜጎች ያማርን ሰብሎች ነን፡፡ ወደ መቶ ሚሊዬን የምንጠጋ በብዛታችን ውስጥ አንድነት ያለ፣ በልዬነታችን ውስጥ አንድ አይነት መቻቻል ያለ ህዝቦች ነን፡፡ እንኳን ዛሬ ዋስትና የሚሰጠን ህግ እና ስርዓት እያለን ድሮ ባላከበረን እና ባዋረደን ስርዓት ውስጥ እንኳን ሆነን የምንናናቅ ህዝቦች አልነበርንም የምንከባበር እና የምንቻቻል ህዝቦች፣ ባህሎች፣ ሃይማኖቶች እና እንድነቶች ነበርን፡፡
ዛሬ ያለው ደግሞ ከትላንቱ ይለያል፡፡ አረሙ ግን ትላንትም ነበር ዛሬም አለ፡፡
ይህ ሰፊው መገለጫችን ሆኖ ግን ደግሞ ከሰብል ውስጥ አረም እንደማይጠፋ ይህ ሰፊ ጸጥታ የማይዋጥላቸው ጥቂት ጫጫታዎች አሉ፡፡ እነዚህ እንደ አረም ናቸው፡፡ መኖራቸውም ተፈጥሯዊ ነው፡፡
እርግጥ ነው ትላንት የነበረው ዋናው አረም ስርዓቱ ነበር፡፡ ያንን አረም የነቀለ ትውልድም በታሪካችን ውስጥ አልፏል፡፡ እነ ጥላሁን፣ እነ ማርታ እና እነዋለልኝ መኮንን የመሩት ያ ትውልድ እስከ ኢህአዴግ ድረስ የመምራት ስልጣን ዞ የነበረውን አረም ነቅለው ለመጣል የቻሉ ናቸው፡፡
ዛሬ ደግሞ አረሞቹ ከስርዓቱ ሳይሆን ህዝቡ ውስጥ የበቀሉ ናቸው፡፡ ትላንት ማሳው ላይ አረም የሚዘራ ሰንፍ ገበሬ ነበር፡፡ ዛሬ ገበሬው ምርጡን ዘርቶ አረሙ ግን ከዘሩ ጋር የተቀላቀለ ጥቂት ነው፡፡
እና ይህንን አረም ማን ይንቀለው? ነው ይያቄው፡፡
እርግጥ የዛሬው ገበሬ ታታሪ ነው፡፡
ግን ደግሞ መታተሩ በዘሩ ላይ ያተኮረ እንጅ አረሙን ለመንቀል ያልበረታም መስላል፡፡ አረሙ ጥቂት ነው ብሎ ንቆ ትቶት ከቆዬ 25 ያህል የአዘመራ አመታት አልፈዋልና እንዲህ ማለቴ፡፡
እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ነጥብ በእነዚህ 25ዓመታት አረሙ በዝቷል ወይስ እየቀጨጨ ሄዷል? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡
ሁላችንንም የሚያግባባን እና ባለፉት 25 አመታት ውስጥ ጎልቶ እያደገ የመጣው ዴሞክራሲ ስርዓት ነው፡፡ ዴሞክራሲው ደግሞ በዋናነት የቀደመውን የህዝቦች እኩልነት፣ መቻቻል እና አንድነት የሚያበረታ እና ለህዝቦች ዋስትና ሊሆን የሚገባው እንደሆነ ግድ ነው፡፡ በኔ እምነት ይህም እየሆነ መጥቷል ባይ ነኝ፡፡ አልፎ አልፎ ግን አረሞቹ ብቅ ብለው ማሳውን ሊያውኩ ሲነሱ የዴሞክራሲው ዋስትና መሆን ያለበት እንዴት ነው? የሚለውን ጉዳይ በጥንቃቄ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ከሰሞኑ ሁኔታ መማር ያለብንም ይህንን ነው፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ዴሞክራሲ ዋስትና ሊሆን የሚገባው ለእኩልነት እና ለሰላም ነው፡፡ ሰላም ደግሞ የሰፊው ህዝብ ዋጋ ነው እና የትግሉ ውጤት ነው፡፡
ታዲያ እንዲህ ከሆነ ይህንን ሰላም ደንገት ብቅ ብለው ከውጭም ታዘዙ ከውስጥ ተነሱ ሊያደፈርሱት ሲሞክሩ ዴሞካርሲ ትእግስቱ እስከምን ድረስ ነው? አረሞችን ለመንቀል ትእግስቱ የት ጥግ ድረስ መርዘም አለበት? ዴሞክራሲስ ዋስትና የሚሰጠው ለሰላም ከሆነ ሰላም የማይፈልጉትን እንዴት ማስተናገድ አለበት የሚለውን በጥንቃቄ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ካልሆነ ከሰፊው ሰላም እና እድገት ባሻገር እንደሰሞኑ ጠባቡን ብጥብጥ ላይ እንዳናተኩር እሰጋለሁ፡፡
የሚያድገውን እና የሚለወጠውን ትልቅ ሃገር ማየት ትተን ትንሹዋን ጫጫታ ብቻ እንዳንመሰጥባት እሰጋለሁ፡፡
ለምን መሰላችሁ፣ “አረም ምንጊዜም አረም  ነው” የሚለውን ከተስማማን አንዲትም የአረም የጥፋት እርዝማኔ በቸልታ ትተን የአንዲትም መልካም ሰብል ደህንነት ስጋት ውስጥ መግባት የለባትም፡፡ እዚህ ላይ ሰሞኑን ሁኔታ ወስደን ካየን ከውጭም ከውስጥም ችላ ተብለው የኖሩት አረም ያልናቸው ጸረ ሰላሞች ዛሬ ከስጋትም አልፈው ህይወት ነጣቂ የነውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ዋናው ሽፋን ለትእግስቱ ዴሞክራሲ እንደመነሻ የተወሰደ ይመስለኛል፡፡
እኔ አረምን የሚታገስ ገበሬ አይነት ነው የሚመስለኝ፡፡ ወይም የዴሞክራሲ ስርዓት ቸልተኝነት፡፡ ለዚህ ነው ዴሞክራሲ ዋስትናው ለህዝቡ እንጅ ለአረሞቹ መሆን የለበትም የምለው፡፡ መቼም በጠንካራ ገበሬ የመሰልኩት መንግስት አረሙንና ሰብሉን መለየት ያቅተዋል ብዬ አላስብም፡፡ እንዲህ ከሆነ ታዲያ ማሳው እስኪቃጠልና ሰብል እስኪጠፋ የሚጠበቀው ለምንድን ነው?
እርግጥ ነው መንግስት የትኞቹ ጸረ ዴሞክራሲ አቋም እንዳላቸው የትኞቹ ደግሞ የማንን አጀንዳ ይዘው ሃገር እና ህዝብ ለማወክ እንደሚሰሩ ይታወቃል፡፡
ከውጭ በጠላቶቻችን ገንዘብ ስፖንሰር እየተደረጉ ከውስጥ ጥይት የሚያስተኩሱ እንማን እንደሆኑ ተለይተዋል፡፡
ግን ደግሞ ጥይት ተኳሾችም አስተኳሾችም በተለዬበት ሁኔታ የመንግስት ርምጃ ሳምንታትን መታገስ ተገቢነቱ ብዙም ነው፡፡
ሰፊው ጸጥታ በጥቂቶች የረብሻ ድምጽ እስኪረበሽ ድረስ ህዝብም መንግስትም መታገስ የለበትም፡፡
ምክንያቱም ዴሞክራሲው እና ልማቱ የሚጠቅመው እና ዋስትና ሚሆነው እንዲሁም በጠንካራ መሰረት ላይ ያቆሙት ትልቁ ሰፊ ህዝብ እንጅ ጥቂት ጠባብና ትምክህተኞች አይደሉም፡፡
ስለዚህ እነዚያን ለማስቆም እና በቃችሁ ለማለት የተጻፈው ህግ ብቻውን በቂ ነው፡፡
እዚህ ላይ አድማጮቼ የሰሞኑን የነዚሁን የጽንፈኛ አረሞች የፕሮፓጋንዳ አጀንዳ ብቻ በማየት አላማቸው ምን እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች እና በጎንደር ጭልጋና መተማ አካባቢዎች ተነስቶ የነበረው ግርግር በመንግስት ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የጽንፈኛው ሚዲያ አጀንዳ የዑዑታ ሆኗል፡፡
ንጹሃን ተገደሉ…..ተገደሉ….ተገደሉ…..የወቀሳ እና የዑዑታ ዜናዎች ናቸው የሚሰሙት፡፡
ይህንን ተለማጀብ ደግሞ እንደ ሰማያዊ እና መድረክ አይነት ፖርቲዎች የውስጥ አርበኞች ሆነዋል፡፡
እርግጥ ነው ንጹሃን በዚህ ግርግር ሞተዋል፣ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል፣ መሳሪያ የታጠቁ አሸባሪዎችም እንዲሁ፣ በሌላ በኩል የልማት ስራዎች ወድመዋል፣ ተሸከሪካሪዎች አምቡላንሶችን ሳይቀር እና የመንግስት ተቋማት ተቃጠይለዋል፡፡ ይህ ሰፊውን ጸጥታ የረበሸ ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ያሳዘነ የጥፋት ድርጊት ነው፡፡
እንግዲህ እነኝህን ሁሉ ጥፋቶች የወያኔ ናቸው በማለት ጽንፈኛው ከውጭ ሲያራግብ የተመዘገቡ ለጥፋት ፊት ኋላ ባዬች ደግሞ ከውስጥ የኢህአዴግ ችግሮች ናቸው እያሉ ነው ከሰሞኑ፡፡
እዚህ ላየ የሰሞኑን ለአፍታ ገታ እናድርገው እና የኖሩበትን የጥፋት ቅስቀሳ አጀንዳ እንመልከት፡፡ ያለፈውን ስንመለከት ሁልጊዜም “ወያኔን ለማጥፋት ተነሱ….ተነሱ…..ተነሱ” የሚል ብቻ ነበር፡፡
በዚህ የተነሱ ዘመቻ ውስጥ ማስነሻ አና ማነሳሻ ናቸው ያሏቸውን በርካታ ወቅታዊ እና የፈጠራ በደሎችን ሲያቀርቡ ኖረዋል፡፡
ለአብነት አማራው ተነስ “ወገንህ ተፈናቀለ”፣ ኦሮሞው ተነስ መሬትህ ተወረረ ሙስሊሙ ተነስ ሃይማኖታዊ ነጻነትህ በወያኔ ተገፈፈ፣ ክርስትያኑ ተነስ ደብርህ እና ክብርህ በወያኔ ተደፈረ እና የመሳሰሉት ጉዳዬች እየተነሱ የተነስ ጥሪ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡
ይህን ጥሪ ሰምቶ እና አድምጦ ነፍጥ ያነሳ አይደለም ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገ ህዝብ ሲያጡ ህዝቡን ስሜቱን ለመቆስቆስ ሰንደቁን እስከማቃጠልም ደርሰዋል፡፡
ያም ብቻ አይደለም በተለያዬ ጊዜ ሃገር ውስጥ ያሉና ስፖንሰር የሚያደርጓቸውን ሰዎች አሰልፈው ረብሻ ለምፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡
እን አልሸባብ ያልቻሉትን እነሱ በእነሱ ሰው ላይ ቦንብ ወርውረዋል፡፡ የተነስ ጥሪያቸው እስከዚህ የዘለቀ ነበር፡፡
ከዚያም ሌላው አልነሳ ሲላቸው ኦሮሚያ ላይ የራሳቸውን አስነስተው ብጥብጥ ጀምረዋል፡፡ ጎንደር ዘልቀው ቅማንቱና አማራውን ለማለያየት እና ለማታኮስ ሞክረዋል፡፡
ተነስ ያሉት ህዝብ አልነሳ ሲል ተነሱ ብለው የራሳቸውን ጥቂቶች አስነስተው ጥቂት ነፍስ ቀጥፈው ባለበት ወቅት ቁጭ እንዲሉ ሲደረጉ ደግሞ አጀንዳው መንግስትን ገዳይ አድርጎ የመክሰስ ሆኗል፡፡
እኔ ምለው ታጥቆ ሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን ጥይት የተኮሰን ጸረ ሰላም መንግስት እንዴት ነበር መከላከል የነበረበት?
እሳት ይዞ አምቡንስ የሚያቃጥለውን መስሪያቤት የሚለኩሰውን አረም እንዴት ነበር መመከት ያለበት?
ከፊት ከኋላ ሆነው ምንም የማያውቁ ህጻናትን እሳት ውስጥ እንዲገቡ የሚገፉትን ጥቂቶች ዴሞክራሲያችን እንዴት ነበር ማስተናገድ የነበረበት?
ህዝብ እና ሃገር ለመጠበቅ የቆመን ፖሊስ ደብድቦ የሚገድልን የውጭ ትእዛዝ ተቀባይ በዴሞክራሲ አግባብ እንዴት ነበር ማስቆም የሚቻለው?
ከውጭ ተነስ ተብሎ የተነሳን ውስጥ መልእክተኛ በሰላማዊ መንገድ እንዴት ነበር መንግስት ቁጭ በል ማለት ያለበት?
እነዚህን ሁሉ ጥያቄዎች ለመመለስ የተነስ ባዬችን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብእና በማየት መመለስ የሚቻል ቢሆንም የውጤቱ መነሻ ግን እዚያው እነሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ጽንፈኘቹ እና ሃሳብ ተቀባዬቻቸው የሃገር ውስጥ ተቃዋሚዎች ተነስ ያሉት ባይነሳም በጥቂቱም ቢሆን ተንቀሳቅሰው ህይወት እንዲጠፋ ንብረት እንዲወድም ግን ምክንያት ሆነዋል፡፡
እሁን ተገደልን እያሉ የሚጮሁት መነሻዎቹ በቢሆኑም ህዝቡ ግን በያካባቢው እየጠየቀ ያለው ለተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች እና ፖሊሶች መነሻ ምክንያት የሆኑት ይታሩልን ነው፡፡
ይህ ከማንኛውም ሃሳብ በላይ ተቀባይነት ያለው እና ለቀጣዬም ትምህርት የሚወሰድበት ይመስለኛል፡፡
የጽንፋው ጅራፍ ያው የታወቀ ነው፡
ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮህ አይነት የወቀሳ እና የውንጀላ ታክቲክ እየተከተለ የጥላቻ ስትራቴጅውን ለማሳካት የሚሮጥ ነው፡፡
የህዝቡ ጥያቄ ግን ወሳኝ ነው፡፡ የውጮቹ ያው ያታወቃሉ፡፡ የቀደመ ስርዓታቸው ወድቆባቸው ከህዝብ ጋር ቁርሾ የገቡት እና ስልጣን ባለማግኘታቸው ህዝቡን ያኮረፉት በዚህም መልሰው ቦንብ የሚወረውሩበት ናቸው፡፡
እነሱን እንተዋቸው፡፡ ከውስጥ ሆነው ግን ሰፊውን ጸጥታ የሚረብሹትን ማስቆም አሁንም የመንግስት ግዴታ ህዝብም ሃላፊነት ነው፡፡
መንግስት እሳት ይዞ የመጣን ከቻለ እሳቱን ካልሆነ ባለ እሳቱን ጨምሮ እንዲያጠፋ ህዝብ የሰጠው ሃላፊነት አለበት፡፡ ይሄ ለህዝብ ጥቅም ሊወጣው የሚገባው ሃላፊነት ነው፡፡
ዴሞክራሲው ዋስትና የሆነው ህዝብ በዴሞክራሲ ስም በበቀሉ ጸረ ዴሞካራቶች ሰላሙ ሊናጋ አይገባውም፡፡

ቀደም ብዬ እንዳልኴችሁ ከዚህ በፊት ተነስ፣ ዝመት፣ ክተት ሲሉ የነበሩ ሚዲያዎች እና ፌስቡከሮች ተነሳ ያሉት ሲቀመጥ ሌላ አጀንዳ ዘርግተዋል፡፡
ዋነኛ ግቡ መንግስትና ህዝብ መሃል፣ ህዝብና ህዝብ መሃል ጥላቻ ለመፍጠር ሲሆን የሰሞኑ የወቀሳ እና የዑዑታ ነው፡፡ አንዱ በቀድሞ የደርግ ሚንስትር የሚመራ ራዲዬ አትላንታ ውስጥ ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት ሊካሄድ ነው ብሎ አውርቶ አድማጮችን ጋብዞ ሲያዛጋ በመዋሉ ሲያዝናናኝ ነበር፡፡
ክቡር ሚንስትሩ በአትላንታ ለ30 ደቂቃ ያህል በራዲዬናቸው ያደረጉት ልመና ሰሚ ማጣቱ ብዙ አልገረመንም፡፡ ይልቁንም የገረመን እርስዎ ፍላጎት ነው፡፡ እንዴ ክቡር ሚንስትር ያ የቀድሞ ስርዓትዎን ማንም መስማት እንደማይፈልግ ከዘህ እንኳን መረዳት አይችሉም እንዴ? 30 ደቂቃ ለምነው አንድ ሰው እንኳን ወደ መስመርዎ የማይገባው ለምን እንደሆነ እንዴት መገመት ይከብድዎታል፡፡
እኔ እርስዎን ብሆን ኖሮ ከ30 ደቂቃው ውስጥ 15ቱን ደቂቃ አይቼ አድምጭ ካልገባልኝ ለምን እትደውሉልኝም ብየ እጠይቅ ነበር፡፡
የውነቴን ነው የቀድሞ ክቡር ሚንስትር እንዲህ አድማጭ ካጡ ለምን ራዲዬንዎች አይዘጉም?
ወይ ደግሞ ያለፈውን ስህተትዎን የሚያነጻ ኑዛዜ ነገር ቢያስደምጡን ይሻል ነበር፡፡ እንዴት ትገሉ እንደነበር፡፡ እንዴት አንድ ታጋይ የኢህአፓ ትውልድ እንደበላችሁ፡፡ እንዴት ከፕሮፊሰር መስፍን ጋር ሆናችሁ አለቃችሁ መንጌን አማራ የሚባል ብሄር የለም እንዳስባላችሁት…..ምናምን ቢያወሩን ይሻል ነበር፡፡
ኩዴታ ምናምን ይላሉ እንዴ ደግሞ?!
ክቡር ሚንስትር ኩዴታ እኮ ድሮ ቀረ! በናንተ ዘመን፡፡ “የህዝባዊ መንግስት ይመስረት” የተማሪውን ጥያቄ ገደል የከተታችሁት ጊዜ ያኔ ቀረኮ - ኩዴታ፡፡
ዛሬማ ህዝብ ራሱ በመረጠው መንግስት ላይ እንዴት ኩዴታ ያደርጋል ብለው ነው ህዝቡን እንወያይ ማለትዎ፡፡ ባይሆን እናንተ ድሮ አለቃችሁ ለስራ ጉብኝት ሲወጣ ትሞካክሩት እንደነበር ግልጽ ነው፡፡
ትላንት እኮ በቃ ትላትንት ቀረ ክቡር ሚንስትር፡፡ እረ በናትዎት ከእንቅልፍዎ ይንቁ፡፡ ወንድሜ ያይቆብ የሚለውን ዘፈን ወንድሜ ሚንስትሩ ጋዜጠኛው ተኝተዋል ወይ ሃገር ተቀየረ ብለን እንቅስቅስዎ እንዴ?!
ለነገሩ ተኝተው እያየን እንዴት ተኝተዋል ወይ ብለን እንጠይቃለን፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ ትላንትን የሚያንቀላፋ ሰው ግን እንዴት ያስጠላል መሰለዎት፡፡ ስለጠላዎት እኮ ነው ዴያስፖራው ራሱ 30 ደቂቃ ግቡኝ አውሩልኝ እያሉ ሲለምኑ ጥላቻውን በዝምታ ያሳየዎት፡፡
ሌላው ለ30 ደቂቃ በናትችሁ ግቡልኝ፡፡ አውሩልኝ እያሉ ሲማጸኑ የራስዎ ደጋፊዎች እንኳን ዝም ያሉት ለምን ይመስልዎታል? አዎ ክቡር ሚንስትር ቢያንስ ለመታመንም ባይሆን ለመሰማት የሚጥም ነገር ማውራት ነበረብዎት፡፡ ሃይለማርያምን በመፈንቅለ መንግስት ሊያነሱት ነው ሲሉ ጽንፈኛው ራሱ ሃሳብ ሊሰጥበት የሚያስፎግረው ነው ብለው ራስወን አጋፍጠው ዝም አሉዎት አይደል፡፡
እኔ ምለው ግን ለደርጉም በዚህ የሙያ ብቃትዎ ነበር እንዴ ማስታወቂያ ሚንስትርን ሲመሩ የነበረው?
አይ ዘመነ ደርግ ስንቱን አሽክላ በሃገር ጭኖ ኖሯል በናታችሁ፡፡
ህልሙን ለመኖር የሚታትር ሰው እንደስዎ መቼም አላየሁም፡፡ እርስዎ አትላንታ ቁጭ ብለው በህልም አለም እየኖሩ አድማጩም ከእርስዎ ጋር ትላንትን እንዲያንቀላፋ ለ30 ደቂቃ ያህል አየር ላይ ይለምናሉ እንዴ?
ዝምባዌ ያሉት የቀድሞ አለቃዎ ራሳቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ቢደውሉላቸው “ባክህ አትቃዥ የምን ኩዴታ ነው፣ የምትቀባጥረው ሊልዎት ይችላሉ፡፡
ለማንኛውም እኔ ልንገርዎ አየር ሰዓቱን ቢያንስ በቀሪ ዘመንዎ ኑዛዜዎን ቢያስተላልፉበት በእርግጥም ጥሩ ነገር በሆነልዎት ነበር፡፡
በቀጣይ ፕሮግራምዎ “ኢትዬጵያ ውስጥ ባቡር የለም ወይስ አለ” በሚለው ጉዳይ ላይ አድማጮችዎን አስተያየት እዳይጠይቁ እሰጋለሁ፡፡
ምናልባት በዚህ ጉዳይ እንደስዎ ያለ እንቅልፋም ከተገኘ በእርግጥ ባገራችን ባቡር አለ ባቡሩ ግን የወያኔ ሳይሆን የሚኒልክ ብቻ ነው” ይልዎት ይሆናል፡፡
ለነገሩ ክቡር ሚንስትሩን እና ሌሎችንም ፌስ ቡከሮች ያልገባቸው ነገር የህዝቡን ሁኔታ ጠንቅቆ ያለማወቅ ነው፡፡
ህዝቡ ሰላሙን ዴሞክራሲውን እና ልማቱን የሚኖረው ፌስ ቡክ ላይ ብቻ የሚመስላቸው ጽንፈኞች ብዙ ናቸው፡፡
ብድግ ብለው ራዲዬናቸው ወይ ፊስቡካቸው ላይ መፈንቅለ መንገስት ሊካሄድ ነው ብለው ይጽፋሉ፡፡ ከሰሞኑ ስናየው የነበረው ደግሞ በጣም የሚያስገርም ነው፡፡
እንዳንዱማ መንግስት ከመቀየሩ ባሻገር ቤተክርስቲያኑንም መስጊዱንም ምንኑም አቃጥሎ ሲያበቃ ፍላጎቱን ፊስ ቡክ ላይ ቁጭ ያደርጋል፡፡
የቀላል ፈንጅ አሰራር እንዴት እንደሆነ የሚመክር ፔጅ ሳይ የሰዎቹን ሃገር የማፍረስ ፍላጎት የቱን ያህለ እንደሆነ ማየት ትችላላችሁ፡፡
ከነዚህ የተሸለ አቅም ያላቸው አንዋር አማኞች ላይ ቦንብ ሲያስወረውሩ አቅም ያጣው ደግሞ ሌሎች ቦንብ ሰርተው እንዲወረውሩ የአሰራር ሜኑ አዘጋጅቶ ለጥፏል፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ ይኸው ፔጅ ባለፈው አንዋር ላይ የፈለነዳውን ቦንብ መንግስት ሆን ብሎ ያፈነዳው ነው ብሎ ለጥፎ ነበር፡፡ እና አሁንስ ጸሃፊውን መንግስት አሰራሩን እንዲለጥብ አስገድዶት ነው እንዴ?
ለማንኛውም አድማጮቼ በዚህ በሰሞኑ ጉዳይ እንደሚንስትሩ ከመቃዥት ባሻገር ገዘፍ ያሉ ውሸቶችንም ስናይ ነበር፡፡ ለምሳሌ ከሁለት ዓመት በፊት የተቃጠለ ቤተ ክርስቲያን ምስል በሰሞኑ ግርግር በሆነ አንድ ብሄር እንደተቃጠለ አድርገው ፎቶ የለጠፉ በዚህም ጫጫታ ፈልገው የተነሱ ነበሩ፡፡
አዲስ አበባ ዬንቨርስቲ ጸጥ ባለበት ወቅት ጥቁር ለብሰው ለሃሰሳ ጩኸት ተማሪዎችን ለመቀስቀስ የሄዱት ሳይካላቸው ቢመለሱም ቅሉ በዬንቨርስቲው ተማሪዎች ግርግር እንደተነሳ አስመስለው ከአመታት በፊት የተነሳን ፎቶ ለጥፈው በገጻቸው ያስነበቡም ነበሩ፡፡
ከሱዳን በመተማ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የነዳጅ ቦቴ ተቃጠለ ተብሎ የተለጠፈው ምስል በላጎስ አየር ማረፊያ በ2011 በፈረንጆች የተቃጠለ ምስል ያሳዬናል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ መነሻቸው ግጭቱን ለማስፋት እና አንዱን ባንዱ ላይ ለማስነሳት የታመኑ መስሎ ለመቅረብ የሚያደርጓቸው ናቸው፡፡
ደግነቱ ግን ህዝቡ የሚኖረው ተግባርን እንጅ ወሬን አይደለም፡፡
ህዝቡ የሚጠቀመው መሬት ላይ ካለው ልማት እና ሰላም እንጅ ፊስ ቡክ ላይ ካለው ጥላቻ አይደለም እና የፌስቡክን ህይወት ለናንተው ትተነዋል፡፡
ፌስ ቡክ ለልማት እና ለህዝብ የሚጠቀሙት ደግሞ በሌላኛው ጫፍ ራቁታችሁን እያስቀሯችሁ ነውና በጊዜ ጠንቀቅ በሉ፡፡
ውድ አድማጮቼ በፌስ ቡክ በራዲዬ በፓርቲዎች አማካኝነት ብቻ በብዙ መልኩ ዴያስፖራው ውስጥ ሆነው ትእዛዝ እየሰጡ ትርምስ እየፈጠሩ ያሉ ጽንፈኞች ቢኖሩም አብዛኛው ኢትዬጵያዊና ትውልደ ኢትዬጵያዊ ግን ዛሬም የሃገሩ ጉዳይ ከኪስ ጥቅም ባሻገር አብዝቶ የሚያስጨንቀው እና ሰላምና ልማትን ለመረጋገጥ አብዝቶ የሚሰራ ነው፡፡
ይህ ብቻም አይደለም በየጊዜው በሚደረጉ ሃገራዊ የልማት ስራዎች ላይ የድርሻውን ከማበርከት ባሻገር አሁንም እዚህና እዚያ ያሉት ጽንፈኞች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በጽኑ የሚቃወሙ ናቸው፡፡
ዴሞክራሲ ዋጋው የህዝብ ሰላም ነው፡፡ ብዛቱ፣ ጥራቱም የሚለካው የህዝብን ሰላም በማረጋገጥ እንጅ የጽንፈኞችን ጽንፍ የወጣ ጥፋት በመታገስ አይደለም!!

03040954
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1038
1650
42067
51980
3040954

Since April 1, 2014

Photo Gallery