Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESኢትዬጵያዊያን ባለሃብቶች በኢትዬ-ጅቡቲ የኢኮኖሚ ትስስር ውስጥ የላቀ ድርሻ እየተወጡ ነው

ኢትዬጵያዊያን ባለሃብቶች በኢትዬ-ጅቡቲ የኢኮኖሚ ትስስር ውስጥ የላቀ ድርሻ እየተወጡ ነው

Published in Articles
Rate this item
(0 votes)

በጅቡቲ የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፖ ቅርንጫፍ ግንባታ የኢትዬ ጅቡቲ የኢኮኖሚ ትስስር ውጤት ነው፡፡
በኢትዮጵያ የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፖ ባለቤት አቶ ታዲዬስ ጌታቸው እና በሃገሪቱ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ስራ ላይ ባላቸው ጉልህ ተሳትፎ የሚታወቁት አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በጋራ ይህንን የሃገራቱን ጥረት በአዲስ መልኩ የሚያጠናክር የኢንቨስትመንት ስራ ጅቡቲ ላይ ጀምረዋል፡፡
ውብ መልካምድራዊ አቀማመጥ ባለው በጅቡቲ ሙቻ ባህረገብ መሬት ላይ የሚገነባው ሪዞርትና ስፖ በሁለቱ ሃገራት መልካም ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት አማካኝነት የተፈጠረ የኢንቨስትመንት ስራ መሆኑን ባለሃብቶች ይናገራሉ፡፡
ታሪካዊ ግንኙነት ያለው የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ እየተጠናከረ እና በበርካታ ዘርፎችም የግል ባለሃብቱን ጭምር እያሳተፈ መጥቷል፡፡
ባለፉት ጊዜያት ኢትዬጵያ በኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ ጅቡቲ ደግሞ በወደብ አቅርቦት በኩል የነበረው የሁለቱ ሃገራት ትስስር በባቡር፣ በመንገድ፣ በውሃ እና በቅርቡም በጋዝ መስመር ዝርጋታ ግንኙነታቸው እየተጠናከረ መጥቷል፡፡
ይሁንና ይህ የሃገራቱ የኢኮኖሚ ትስስር ለሃገራቱ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር የሆነውን የግል ባለሃብት በማሳተፍ ተግባራዊ ሲደረግ የሪዞርት ግንባታው ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው ማለት ይቻላል፡፡
በጅቡቲ በሙቻ ባህረ ገብ መሬት ላይ ዘመናዊ ሪዞርትና ስፖ ለመገንባት የኩሪፍቱ አቶ ታዲዎስ ጌታቸው እና አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በጋራ የሚገነቡት ውብ ሪዞርት ከ7 ሚሊዬን አሜሪካን ዶላር በላይ ወጭ ይጠይቃል፡፡
የዚህ ዘመናዊ እና ውብ መዝናኛ ግንባታ በአንድ አመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግንባታው እየተፋጠነ መሆኑን ከባለሃብቶቹ ያገኜነው መረጃ ያሳያል፡፡
የሪዞርት ግንባተውን በስፍራው ተገኝተው የመረቁት እና የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ፕሬዘዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጅቡቲና ኢትዬጵያ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት እያሳደጉ በኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸውን ትስስር ይበልጥ እያጠናከሩ እንደሚሄዱ ያላቸቸውን እምነት ይገልጻሉ፡፡
ጅቡቲ ላይ ስራቸውን ጀመሩት ሁለቱ ባለሃብቶችም ስራቸው ከግል ኢንቨስትመንት ባሻገር ለሌሎች ባለሃብቶችም አርዓያ ሊሆን የሚችል እንደ ሃገርም የተያዘውን ወዳጅነት ጉዞ በልማታዊነት የሚያጠናክር እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
አሁን አሁን በሃገራችን የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ልማቱን የሚደግፉ ባለሃብቶች በተበራከቱበት ሁኔታ ዲፕሎማሲያችን በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ደግሞ የመንግስትን ጥረት የሚደግፉት እንደ አቶ ዳዊት አይነት ባለሃብቶች የአዲሲቷ ኢትዬጵያ የእድገትና የብልጽግና መሰረት ናቸው፡፡
ባለሃብቶቹ የሚገነቡት ሪዞርት ስራ በቀጣዬቹ ወራት ሲጠናቀቅ 30 ፕሬዘደንሽያል ስዊት፣ 120 አልጋዎች እና የተለያዬ ቪላዎች እንደሚኖሩት ለማወቅ ተችሏል፡፡

03040958
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1042
1650
42071
51980
3040958

Since April 1, 2014

Photo Gallery