Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESፖለቲካና ኤሌክትሪክን በሩቁ…

ፖለቲካና ኤሌክትሪክን በሩቁ…

Published in Articles
Rate this item
(0 votes)

(በቴዎድሮስ ታደሰ) “ፖለቲካና ኤሌክትሪክን በሩቁ” የሚል አባባል መቼና እንዴት እንደተፈጠረ በዚያ ትውልድ የተወለዳችሁ ሰዎች በተለይ ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ አባባሉም አዲስና እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ብቻ እንዲሁ በብዙው ወጣት ላይ ፍርሃት እንዳጫረ ከግምሽ ክፍለ ዘመን በላይ አስቆጥሯል፡፡
ለዚህ ትውልድ ከቃሉ ጥሬ ትርጉም በላይ ለምን የት እና እዴት ይህ አባባል ተጠረ የሚለውን ለማስረዳት ከመሞከሬ በፊት ሰሞኑን አንድ መድረክ ላይ ተገኝቼ ስለነበረ ነው ሃሳቡን ደጋግሜ ሳኝክ አንድ እውነት የተገለጠልኝ የመሰለኝ፡፡
ለማንኛውም ይህች ፍርሃትን የምትሰብክ አባባል የተፈጠረችው በ1960ዎቹ የተማሪውን ንቅናቄ ተከትሎ በኢትዬጵያ እየተቀጣጠለ የመጣው የኢትዬጵያ ወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የእድገትና የውድቀቱ ውጤት ከሆኖት እሳቤዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ተማሪዎች ተቀጣጥሎ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተቀላቅለውት የአጼውን ስርዓት ያናጋው አመጽ አጼውን ጥሎ የስልጣን ወንበሩ በወታደሩ እጅ ሲወድቅ የኢትዬጵያ ወጣቶች አምባገነንነትን በዝምታ  አልተቀበሉም፡፡
ይልቁንም በወቅቱ የህዝብ አስተዳደርን ለመመለስ እና ዴሞክራሲን ለማስፈን አዋጭ ናቸው ባሏቸው አደረጃጀቶች ውስጥ የወጣቱ ተሳትፎ ጉልህ ነበር፡፡
በዚያን ጊዜ በተለይም ወጣቱን በማሰባሰብ በህቡእ ይንቀሳቀስ የነበረው ኢህአፓ ለውጥ ያመጣል በሚል በብዙዎች ተስፋ የተጣለበት ድርጅት ነበር፡፡
ይሁንና ያ ግዙፍ አደረጃጀት በራሱ የውስጥ ችግር መፍረክረክ ሲጀምር የቀይ ሽብር ጡጫም ሲበረታ መበታተን ጀመረ፡፡
ኢህአፓን አምነው ለትግል የተሰለፉትም የደርግ ቢላ ሰለባዎች ሆኑ፡፡ ጎዳናዎች የወጣቶች በድን የማይታጣባቸው የትራጄዲ መድረኮች ሆኑ፡፡
በዚህና በሌሎችም የደርግ ግድያዎች መንግስቱ አለም አቀፍ ገዳይ መንግስት ሆነ፡፡ በቅርቡም ትሩዝ ኮድ የተባለ ድረ ገጽ ያወጣው መረጃ 1.5 ሚሊዬን ዜጎችን በመግደል መንግስቱ ሃይለማርያም ካለማችን 10 ገዳይ መሪዎች አንዱ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
በቀይሽብርና በሌሎችም ግድያዎቹ መንግስቱ ሃይለማርያም ከነ ስታሊን እና ሂትለር ተርታ የተሰለበትን ጨካኝ እንዲሆን አስችለውታል፡፡
እንግዲህ የያኔው የኢህአፓ አመራር ከዚያ ሁሉ መስዋእትነት በኋላ ራሱን አርሞ በዴሞክራሲያዊ አኳኳን ታግሎ ከማታገል ይልቅ አባላቱን አስበልቶ ፖለቲካና ኤሌክትሪክን በሩቁ ብሎ በሱዳን ወደ አሜሪካና መሰል ሃገሮች ፈረጠጠ፡፡
እንዲያ ብለው ሁሉንም ነገር ርግፍ አድርገው የሚኖሩት እንዳሉ ሁነው አሁንም ግን በዚህ ስትራቴጅ(ከከ40 ዓመት በፊት ባነሱት መፈክር ማለቴ ነው) አሁንም የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ የሚሞክሩ መሆናቸውን ማየት ይቻላል፡፡
ያኔም ቢሆን ጠላትና ወዳጃጀውን ጥርት ባለ አላማ መለየት ያልቻሉት ኢህአፓዎች ከህወሃትና ከሌሎችም ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር ይዋጉ ነበር፡፡
ዛሬም ካገኙት ጋር እኛ ብቻ እናውቃለን በሚል መርህ የሚላተሙት የኢህአፓ አባላት በግንቦት 7 ተገልብጠው እናውቅልሃለን ማለታቸው ነው፡፡
እኔም የገረመኝ ግን ያኔ ባራመዷት ፖለቲካን በሩቁ መፈክር ዛሬም ታግለው ለማታገል የሚሞክሩ መሆናቸው ነው፡፡
አሜሪካ ሆነው ኢትዬጵያ ውስጥ ሊዋጉ የሚፈልጉ የሩቅ አዝማቾች ናቸው፡፡
የድርጅቱ መሪዎችን ማንነት ስመለከትም ያረጋገጥሁት ይህንኑ ነው፡፡ ዋና ዋናዎቹ ድሮም በኢህአባ ጊዜ ያመኗቸውን ከድተው የፈረጠጡ ናቸው፡፡
ፍርጠጣቸው ሳያሳፍራቸው ግን በሩቁ ሆነው ለዚያውም ዜግነታቸውን ቀይረው በዜግነታችን ሊቆምሩ ሲሞክሩ ነው የምናያቸው፡፡ አንዳንዶቹም የሞቀ ኑሯቸውን በውጭ አመቻችተው ኑሯችሁ አልሞቀም የሚሉ አይነት ናቸው፡፡
እና እንዲህ ያሉትን እና መሰል ጉዳዬጭን ሳስተውል ዛሬም ቢሆን ተነስ፣ ታጠቅ፣ ተሰለፍ የሚሉን የቀድሞ ኢህአፓዎች ለራሳቸው ግን “ፖለቲካንና ኮረንቲን በሩቁ” ከሚለው ያረጀ መፈክራቸው የተላቀቁ አልመሰለኝም፡፡03040990
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1074
1650
42103
51980
3040990

Since April 1, 2014

Photo Gallery