Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESሰላምም ጦርነትም አያስፈልግም

ሰላምም ጦርነትም አያስፈልግም

Published in Articles
Rate this item
(0 votes)

(በጽናት ራዲዬ)
ሰላምም ጦርነትም አያስፈልግም “No peace No war” ስትራቴጂ የኢትዮጵያ ጠላቶች አንደኛው መገለጫ ነው።
ከአመታት በፊት በሻእቢያ እንደተያዘ የሚታመነው ይህ አቋም ኢሳያስ ሳይወድ በግድ የሚያራምደው አቋም ሲሆን ለአተገባበሩ ግን አሁን ላይ እሱ ብቻውን ቀጥተኛ ተሳታፊ አይደለም። ጦርነት ያለመፈለግ ሰላምም ያለመሻት ስትራቴጅውንም የሚፈጽሙት በርካታ ተላላኪዎች ተዘጋጅተዋል።
ሃሳቡን በግርድፉ ስንመለከተው እርስ በእርሱ የሚጋጭ ይመስል ይሆናል። ጦርነት እና ሰላም ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ናቸው። ሁለቱንም ያለመፈለግ ስትራቴጂ መከተል  በራሱ ግራ አጋቢም ይመስላል። ምክንያቱም ጦርነት የማይፈለግ የትኛውም ሰው፣ አካል፣ ቡድን ወይም መንግስት ሰላማዊ ነው ሊባል ይችል ይሆናል።
በሌላኛው ጫፍ ግን ሰላምንም አልፈልግም ሲል መታየቱ ወይም በተግባሩ ሰላምን ለማረጋገጥ ሲሰራ አለመታየቱም እንዲሁ ጦርነት ናፋቂ ሊያስብለው ይችላል - ዝምብለን በግልቡ ካየነው።
ነገር ግን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ካቅማቸውም ከፍላጎታቸውም በመነሳት ጉዳዬን አስፍቶ ለተመለከተ በጦርነትም ሆነ በሰላም ሃሳቦች ላይ ያላቸው አቋም ተመሳሳይ ይሆናል። ተመሳሳይነቱ ደግሞ የጥፋት፣ የነውጥ እና የጥላቻ አላማን የማስፈፀም አቋም እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
ከዚህ አንፃር የጥላቻ ካምፑን ዋና አዝማች(ሻእቢያን) ስንመለከት ግቡ ኢትዮጵያን የማተራማስ ቢሆንም ከአቅሙ በመነሳት ግን ጦርነቱንም ሰላምንም ያለመፈለግ ስትራቴጂውን በኢትዮጵያ ላይ ከያዘ ከደርዘን አመታት በላይ ተቆጥረዋል ማለት ይቻላል።
እዚህ ላይ መመለስ ያለበት ጥያቄ ለምንድን ነው ሰላምንም ጦርነትንም በጣምራ የማይፈልገው ነው የሚለው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህንን አቋም ጭፍራዎቹ እና ተላላኪዎቹ እነ ግንቦት 7፣ ኦብነግ ኦነግና እና ሌሎችም አሸባሪ ድርጅቶች ይህንን አቋም ይጋሩታል።
ሻእቢያ ዛሬ ላይ በአስተሳሰብም በተግባርም ውጤት በማጣት አርጅቷል፡፡ ህዝቡንም ወደ ተስፋ መቁረጥ ወለል ያወረደ የቁልቁለት ጉዞ እየተከተለ ነው፡፡ ይህንን የቁልቁለት ጉዞውን እያፋጠኑት ያሉ ደግሞ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡
ኤርትራዊያን እንደዜጋ በሪፈረንደም ነፃነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ በሰላማዊ ጉርብትና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለመኖር ያላቸውን ፍላጎት በተለያዩ ጦርነቶች ማሰናከል የጀመረው የሻእቢያ አስተዳደር የጦርነት አላማዎቹ ሁሉ ከጥጋብና እብሪት የመነጩ እንደነበሩ በየጊዜው ያደረጋቸው ወረራዎች ማሳያዎች ናቸው፡፡
በዚያ የጀብደኝነት ጦረኛ አስተሳሰቡ አስቀድሞ በየመን እና በጀቡቲ ሲተነኩስ የቆየውን ጦርነት በኋላ ላይ በኢትዮጵያ ላይም ባልተጠበቀ ሁኔታ አስኪዶታል። ያኔ የኢሳያስ አገዛዝ ጦርነትን የሚፈልግ ሰላምን ደግሞ የማይፈልግ ነበር።
ከጦርነቱ ማግስት ከደረሰበት የሞራል የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ክስረት በኋላ ግን የሻእቢያ ስትራቴጁ ተቀይሯል። በተለይም ኢትዮጵያ በብዙ ብሔረሰቦች ተዋጽኦ እድገቷ እየተረጋገጠ፣ በኢኮኖሚና በሰላም ማስከበሩ ዘርፍ አቅሟ ይበልጥ ሲፈረጥም ሻእቢያ ስትራቴጂውን በሽንፈት እንዲቀይር ተገደደ፡፡
ጦርነቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ በኤርትራ ላይ ያመጣው ጉዳት ብቻም አይደለም የአስመራውን ሰውዬ እንዲደነግጥ ያደረገው ይልቁንም የጀብደኝነት ሞራሉ እና የአሸናፊ ነኝ ባይ ድንፋታው በኢትዮጵያ ሰራዊት ሲደፈቅ ለህዝቡ የሚለው ነገር አልነበረውም። ስለዚህ የአምባገነንነት አገዛዙን ይበልጥ በማጠናከር ወጣቱን በማስጨነቅ እንዳይጠይቅ የማድረግ አካሔዱን ተያይዞታል።
በኤርትራ የሚኖር ዜጋ የኢሳያስን አስተዳደር በየትኛውም መልኩ ሊጠይቅም ሆነ ሊተች በአይችልም። ያን ለማድረግ የሚፈልግ ከሆነ ግን “ንቁና ድንጉጥ ታዛዥ” እስኪሆን ድረስ ይቀጠቀጣል።
ወደ ዋናው ነጥቤ ስመጣ የኢትዮጵያ ሽቅብ በኢኮኖሚና በወታደራዊ አቅም ማደግና ከራሷ አልፋ ለሌሎች በሰላም ዘብ መቆም ስትጀምር በሌላ በኩል ኤርትራ ደግሞ በኢሳያስ አገዛዝ ጉዞዋ ቁልቁል ሆነ  ማለት ነው።
ከዚህ ባሻገርም የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ጉዳይ ላይ የያዘውን አቋም መቀየሩን በግልጽ ይፋ ሲያደርግ ከድህነቱም በላይ ውሳኔው የአስመራውን ሰውዬ እንዳደናገጠው አይጠራጠርም።
ከዚያ በፊት ሻእቢያ በኢትዬጵያ ላይ የሚወስዳቸውን የትንኮሳ ተግባራት በመከላከል ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር፡፡ በአዲሱ ውሳኔ መሰረት ግን ራስን ከመከላከል ባሻገር ተመጣጣኝ ርምጃ እንደምትወስድ ይፋ አደረገች፡፡ ይህም በተግባር ታዬ።
ድሮ ድሮ ጠብ ያለሽ በዳቦ ብሎ በጀብደኝነት ጦር ይመዝ የነበረው ሻእቢያ ጉዱን ደብቆ ዝም አለ። እንኳን ፊት ለፊት ሊገጥሙት አስፈሪነቱን እንዲሁም በሩቁ የሚረዱት የኢትዮጵያ ሰራዊት አደረጃጀት ለኢሳያስ ያለጥርጥር አስፈሪ ነው፡፡ ለዚያውም በደቀቀ ኢኮኖሚ እና በኢ-ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ የተዳከመ ሰራዊት ላለው ሻእቢያ ህዝባዊ መሰረት ያለው እና ለህዝብ የወገነው የኢትዬጵያ መከላከያ አስፈሪ ነው።
ለነገሩ አብዛኛው ወጣትስ ከኋላው የሚተኮስበትን የሻእቢያ ጥይት ተቋቁሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት እየሔደ አይደል?
ብቻ በዚህም ተባለ በዚያ ኢሳያስ በአሁኑ ወቅት በበርካታ ምክንያቶች ጦርነት አይፈልግም።
ጦርነት አይፈልግም ማለት ግን ሰላም ይፈልጋል ማለት አይደለም። በጎረቤት ሀገራት በተለይም በኢትዮጵያ የእድገትና የልማት ጉዞ ላይ ያለበትን ደንፎ የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የተለያዩ ጥረቶችን ማድረጉ አልቀረም።
ሻእቢያ በኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ ላይ አሻጥር የሚፈጽም መንግስታዊ አሸባሪ መሆኑም ይታወቃል።
የእናት ጡት ነካሽ የሆኑትን በኢትዮጵያውያን ስም የተደራጁት አሸባሪ ቡድኖች ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት 7 እና ወዘተ አባዎራቸው ሻእቢያ ነው።
የአዞ እንባ ሲያለቅሱ እንባቸውን የሚያብስላቸው ጩኸታቸውን የሚያስተጋባላቸው፣ እና ለጥፋት ሲነሳሱ ጸጉራቸውን የሚያሻሽላቸው የጥፋት አባታቸው ነው፡፡
እንግዲህ ንዚህ ሃይሎች ባንድም ሆነ በሌላ አጋጣሚ መነሻቸው ይለያይ እንጅ አሰላለፋቸው ግን ተመሳሳይ ነው፡፡
ምንም አይነት የተልእኮ ልዬነት ሳይኖራቸው የሚፈጽሙት የማጠልሸት አላማ ነው ያላቸው፡፡
ሁላቸውም ቦሆኑ ጦርነት እና ሰላም የማይፈልጉ ናቸው፡፡
ምክንያቱም ደግሞ ቀደም ሲል ያነሳነው ነው፡፡  ከፊት አውራሪያቸው ጀምሮ ምንም እነት አቅም ስለሌላቸው ወደዚያ ሊያስቡ አይችሉም፡፡ ይሁንና ሰላምን ለማደፍረስ ግን በተለያዬ መልኩ ሲሰሩ እያየናቸው ነው፡፡
ፈንጅ ከማፈንዳት፣ የህዝብና የመንግስት ተቋማትን ለማውደም እና የመንግስት መሪዎችን ለመበግደል ከማሴር ጀምሮ ሁሉንም አይነት የጥፋት ስልቶችን ለመጠቀም ባለፉት ጊዜያት ሞክረዋል፡፡
አንዱም ሳይሳካላቸው ከህልምና ምኞት ሳይዘል የፌዴራል ፖሊስ መዳፍ ውስጥ ይወድቃሉ እንጅ እቅዳቸው ብዙ ነው፡፡
ማንኛውንም አይነት ስልት ተጠቅመው ሃገር ለማተራመስ እና ሰላም ለማሳጣት ይማስናሉ፡፡ ያም ሆኑ በህዝብ እና በመንግስት ጥረት እየተተፉ የመጡ ቡድኖች ሆነዋል፡፡
በዚህ ጽሁፍ ማንሳት የፈለግሁት ዋናው ነጥብ ሰላምንም ጦርነትንም የማይፈልጉት እነዚህ የሃገርና የህዝብ ጠላቶች ምክንያታቸው የተለያዬ ቢሆንም እቅዳቸው ግን አንድም ቀን ግቡን ባግባቡ ሲመታ አልተስተዋለም፡፡
እዚህ ላይ ይህ ለምን ሆነ ብለን መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡
ባለፉት ዓመታት በኢትዬጵያ እየታዬ የመጣው ተከታታይ እና ፈጣን እድገት ህዝቡ በስልጣኔ የትላንቱን ታላቅነት ለመመለስ እንደሚችል ያለውን ተስፋ የፈነጠቀ ነው፡፡
በማንም የማይቀለበስ እና ወደ ኋላም ሊመለስ የማይቻል የሆነ ታላቅ ልማት በራስ አቅም ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
ይህንን ፈርጀ ብዙ የልማት እድገት ደግሞ ብቻውን የመጣ ሳይሆን ሁሉን አሳታፊ በሆነ ዴሞክራሲ ታግዞ የተመዘገበ እድገት ነው፡፡ ጥህንን ማንም ኢትዬጵያዊ ያለነጋሪ በግልጽ ይረዳል፡፡
ሰላምን ከማረጋገጥ አንጻርም ኢትዬጵያዊ ሁሉ በቆዬ ባህሉ እና ለሃገሩ ዘብ መቆመ ዝግጁነቱ ማንንም ወሮ በላ አሸባሪ ከመጋፈጥ ወደኋላ እንደማይል በተለያዬ አጋጣሚዎች አሳይቷል፡፡
የሃገር መከላከያም ሆነ የፌዴራል ፖሊስ መቼም የማይዘናጋ ዝግጁነት ውስጥ በመሆኑ ከልማቱም ባሻገር የሰላም ዘብ ለመሆን ችሏል፡፡
የደህንነት ስራውም ድንበር ተሻግሮ አሸባሪን ከየትም የሚለቅም ሃይል መሆኑ የጥፋት ካምፑን በፍርሃት እያርበደበደው እንዳለ ማየት ይቻላል፡፡
ለዚህም ነው እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ አይነቱን በህዝብ ላይ እሳት ለመጫር የሚሞክር አሸባሪ እያነቀ ማምጣት የቻለው፡፡
ከህግና ከስርዓት በላይ ማንም መሆን እንደማይቻለው የሚያሳዬ በርካታ ድርጊቶች በሃገራችን እየተፈጸሙ ነው፡፡
በነገራችን ላይ የግንቦት 7 መዋቅርም ሆነ የሌሎቹ የትም የማይደርስ እንደሆነ በየጊዜው እየታዬ መጥቷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንትም የነ አንዳርጋቸው ጽጌ የሽብር ተዋጊዎች ተፈርዶባቸዋል፡፡
የአሸባሪው የግንቦት ሰባት ድርጅት የወታደራዊ ጋንታ አዛዥ በመሆን ሲሰራ የቆየውና በድርጅቱ የተመለመሉ ሶስት አባላትን የኢትዮጵያን ድንበር አሻግሮ ወደ ኤርትራ ሊያስገባ ሲል በቁጥጥር ስር የዋለው ታደሰ በላይ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

ተከሳሾቹ 1ኛ ታደሰ በላይ፣ 2ኛ ቢራራ ጨቡድ 3ኛ፣ ፋንታው ጀንበር እና 4ኛ አልዬ ጌትነተ ናቸው።

የአቃቤ ህግ የክስ መዘገብ እንደሚያስረዳው 1ኛ ተከሳሽ የሆነው ታደሰ በላይ ህገ መንገስቱንና ህገ ምንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ለመገርሰስ በማሰብ ቀኑ በውል በማይታወቅበት ከታህሳስ ወር 2004 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ከሌሎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ግንቦት ሰባት የተባለውን የሽብር ቡድን ተቀላቅሏል።

መዝገቡ ቡድኑን ከተቀላቀለ በኋላ ሶስት ወታደራዊ ስልጠናዎችን የወሰደ ሲሆን፥ የሽብር ቡድኑ የጋንታ ምክትል አዛዥ በመሆን ተመድቦ የሰራና መጋቢት 5 ቀን 2005 አ.ም ደግሞ ከሽብር ቡድኑ የበላይ አመራሮች በተላለፈ ትእዛዝ መሰረት ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ስማዳ ወረዳ ተመልምለው ወደ ኤርትራ በመግባት ላይ የነበሩትን 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችን ወደ ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል በድብቅ ገብቶ ማይካድራ በሚባል ቦታ ላይ ተቀብሎ ወደ ኤርትራ ለመግባት ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉን በማስረዳት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በአመራርነት በማገልገል መከሰሱን ነው የሚገልፀው።

2ኛ ተከሳሽ ደግሞ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሽን እየመራ ማይካድራ በተባለ ቦታ ደርሶ እየጠበቃችው ለነበረው ለ1ኛ ተከሳሽ ለማስረከብ ሲንቀሳቀስ መጋቢት 8 ቀን 2005 በቁጥጥር ስር ውሏል።

3ኛ ተከሳሽ በግንቦት ሰባት መልማይ አባል ተመልምሎ ከዚሁም ግለስብ 300 ብር ተቀብሎ በቀጣይም ከ2ኛ   እና ከ4ኛ ተከሳሾች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ድንበር በህገወጥ መንገድ ለማቋረጥ እና ወደ ኤርትራ ለመግባት ሲንቀሳቀስ ማይካድራ በተባለ ቦታ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት በቁጥጥር ስር ውሏል።

4ኛ ተከሳሽ በግንቦት ሰባት ተመልምሎ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠናዎችን ለመውሰድ ከ2ኛ  እና ከ3ኛ ተከሳሾች ጋር የኢትዮጵያን ድንበር ለማቋረጥ እና ወደ ኤርትራ ለመግባት ሲንቀሳቀስ ማይክድራ በተባለ ቦታ መጋቢት 8 ቀን 2005 በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአጠቃለይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጀት ውስጥ መሳተፍና አባል መሆን ወንጀል ተከሰዋል።

ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያሉትን ተከሳሾች እያንዳንዳቸውን በ4 ዓመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራት ሲቀጣ፥ 1ኛ ተከሳሽን ደግሞ በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
የፋና ብሮድካስቲግ ዘገባ እንደሚለውም የኦብነግ አሸባሪዎችን የተመለከተው መዝገብም እንዲሁ በፍርድ ቤት መታየት ጀምሯል፡፡ ከህግና ከስርዓት በላይ መሆን የሚቻለው ማንም የለም፡፡ ሰላምም ጦርነትም አያስፈልግም “No peace No war” ስትራቴጂ የትም እንደማያደርሳቸው ለአሸባሪ ድርጅቶች ትላንትም ዛሬም እያዬት የመጡት ሃቅ ነው፡፡ ኢትዬጵያ የእድገት ጉዞዋን አሸባሪዎችም የቁልቁለት ጉዟቸውን ቀጥለዋል፡፡
ጥፋት በልማት እየተደፈቀ
ድህነት በእድገት እየተሳቀቀ
ኢህአዴግ በሻእቢያ እየሳቀ
ተላላኪ ተኩላዎች ቁልቁል እየተንፏቀቀ
እድገታችን እና ሰላማችን ይቀጥላል፡፡

03040996
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1080
1650
42109
51980
3040996

Since April 1, 2014

Photo Gallery