Solomon Tekalign Interview with Elias Melaku (Ethiopian Embassy)

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዬጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ ሚኒስትር ዲፓርትመንት ኮንሱላር የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ 

 

 

Follow Us

You are here: HomeARTICLESትርጉም በሌለው መጯጯህ የሚግባቡት እንስሳት ብቻ ናቸው!!

ትርጉም በሌለው መጯጯህ የሚግባቡት እንስሳት ብቻ ናቸው!!

Published in Articles
Rate this item
(0 votes)

ከጽናት ራዲዬ -  ታላቅነት ከየት ይጀምራል?
ታላቅነትን እውነትን እና ሃቅን የምንለማመደውስ እንዴት ነው?
የሚወዱትን ሲሸሹ የሚፈርሩትን የሚያቀርቡ አባቶች ተበራክተዋል፡፡
አለመማር ሃጥያት ባይሆንም ሳይማሩ የተማሩ መስሎ መታየት፣ አሊያም አቅምን አውቆ ከራስ ጋር እንደመታረቅ ከህሊና ጋር በማስመሰል ቅዥት የተቃቃሩ ሰዎችስ ይታጣሉ ብላችሁ ነው፡፡
የልጆቻቸውን ፈታኝ ጥያቄ ላለመመለስ አሊያም ከልጁ ጋር በእንግሊዘኛ ችሎታው ላለመፈተን ልጁ እስኪተኛ የብርጭቆ አንገት አንቆ የሚያመሽ አባትም በርከት ብሏል፡፡ ግን ድግሞ የብርጭቆ ወገብ እየጨመቀ ምሁር ለመምሰል የሚሞክር፡፡
የሚገርመው ግን እነዚህ አባቶች ለልጆቻቸው የሚያውቁትን እውነት እየነገሩ በግልጽነት ልጆቻቸውን ከማሳደግ ይልቅ በየመሸታ ቤቱ፣ በየአደባባዬ እና በየፓል ቶኩ ግን ጨርሰው የተራቀቁ ምሁራን ሆነው ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ታሪክ ሊተነትሉ ሲጣጣሩ እናስተውላለን፡፡
መቼም እዚህ ሃገር የምንኖር ኢትዬጵያዊያን እንደ መልካችን አስተሳሰባችንም የብዙዎቻችን ይለያያል ብዬ አስባለሁ፡፡
በአመለካከት ብቻ ሳይሆን በጥረት እና ኑኖን ለማሸነፍ፣ ለማደግ፣ ለማወቅ እና ለመሳሰሉ ጉዳዬችም ጥረቱ የአንዱ ካንዱ በብዙ ይለያል፡፡
አንድ ጽሁፍ ላይ ያነበብሁት ያንድ ታዛቢ አስተያየት ሁላችንንም በጅምላ በሶስት ምድብ ይፈርጀናል፡፡
አንደኛው ምድብ እንቅልፍ አጥቶ እየሰራ የራሱንና የቤተሰቡን ኑሮ ለመለወጥ ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚለው ነው፡፡ እዚህ ግሩፕ ውስጥ ሃገሩን የናፈቀ፣ ገንዘቡን ሰብሰብ አድርጎ ወደ ሃገሩ መመለስ የሚፈልግ እና ነገን ጥሩ ለማድረግ በተስፋ እና በስኬት የሚሰራ ነው፡፡
ሁለተኛው ምንም የማይደንቀው ለእለት ጉዳዬቹ ብቻ የሚጨነቅ ስለዛሬ ኑሮ ዛሬን ብቻ ለመኖር የሚሻው ነው፡፡
ሶስተኛው ደግሞ አማራሪው ነው፡፡ የአሜሪካን ስልጣኔ እያየ ሃገሩ በጥንታዊ ዘመን እንዳለች እና ከመቼውም ጊዜ በከፋ ኋላ ቀር እድገት ውስጥ እንደምትገኝ እያሰበ የሚያብጠለጥል ነው፡፡
የስርዓት ለውጥም አጥብቆ የሚሻ እና በተለያዬ ምክንያት ያኮረፈ እና የትላንቱን እየሻተ የዛሬውን የሚያጣጥል ግሩፕ ነው - በተስፋ መቁረጥ እና በግዴለሽነት ሃገሩን ወደ መካድ የተቃረበም በዚሁ ክፍል አይጠፋም፡፡
በዚህ አካሄድ ከዚያም ከዚህም የሚያገኜው መረጃ እያደናገረው አሊያም ያገኜውን መረጃ ሁሉ እንደወረደ ሳያላምጥ የሚመጥ እና በዚያም ግራ የሚጋባ መሃል ሰፋሪም አይታጣም፡፡
በተለይ በ3ኛው ክፍል ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ባንድም በሌላም ምክንያት ከሃገር ከወጡ 20 እና 30 ዓመታትን ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ ስራ መስራትም ብዙዎቹ አይመቻቸውም በመላላክ በሚያገኙት ገቢ ይኖራሉ፡፡
እነዚህን አይነቶቹ በአንዳች አይነት ስብስብ ውስጥ ታጥረው ሃገራቸውን ለማማት የተፈጠሩ ብቻ ነው የሚመስሉት፡፡
የስራ እንቅስቃሴያቸው የተወሰነ በመሆኑ እና ከመሰሎቻቸው ጋር ተገናኝተው በሃገር ሃሜት ቁዘማ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከማሳለፋቸው የተነሳ በእርግጥ 20 እና 30 ዓመት በኖሩበት አሜሪካ ከልጆቻቸው ጋር መግባቢያ የሚሆን ቋንቋ እንኳን ለማወቅ ተነሳሽነቱም፣ ፍላጎቱም፣ እውቀቱም የላቸውም፡፡
እናም ከልጆቻቸው ጋር በዚህ ሂደት መግባባት የሚያቅታቸው ወላጆችን ማስተዋል ችያለሁ፡፡ ስለዚህ እነዚህ አይነት ሰዎች የልጆቻቸውን ጥያቄ ማስተናገድ ሲያቅታቸው የተለያዬ አማራጮችን ይጠቀማሉ፡፡
አንደኛው ቀደም ብየ እንዳልኋችሁ የመለኪያ ወገብ እየጨመቁ የኢህአዴግ አመራሮችን ማብጠልጠል ነው፡፡
ያነሳነውን ርእሰ ጉዳኝ አስቂኝም አዝናኘም አሳዛኝም የሚያደርገው ይሄ ነው፡፡
በቀላሉ መግባባት፣ በሰለጠነ አለም እየኖሩ አንድም ቀን እንደሰለጠነ ሰው አስበውም ኖረውም የማያውቁት የዲያስፖራው አክራሪዎች  የሃገራቸውን ስርዓት ለመተቼት ግን ባንድ ጊዜ ምሁራን ሆነው ቁጭ ይላሉ፡፡
ራሳቸውን የፖለቲካ ተንታኞች አድርገውም ያቀርቡታል፡፡
20 እና 30 ዓመት እዚህ ሃገር ኖረው ቋንቋ እንኳን በትክክል ለመናገር እውቀቱ የሌላቸው ሰዎች ሃገሪቱ የምትመራረው ባልተማሩ ሰዎች ነው ሲሉ እናደምጣቸዋለን፡፡
የኬጅ ትምህርት የሚከታተሉ ልጆቻቸውን ጥያቄ ለመመለስ አቅም የሌላቸው ሰዎች የሃገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ እና አፈጻጸም ላይ ትንታኔ ለመስጠት ሲስተዋሉ ሰነባብበተዋል፡፡
በነገራችን ላይ እንደዚህ አይነቶቹ አክራሪ ዲያስፖራዎች ሃገር ቤት ቢሆኑ በትክክል የምነግራችሁ አንዳንዶቹ የጎልማሶች ትምህርት መከታተል የሚኖርባቸው ናቸው፡፡
በእነሱ እድሜ እና ከነሱም በላይ ያሉ የሃገር ቤት ወገኖቻቸው ቢያንስ መሰረታዊ ቁም ነገሮችን በጥራዝ ነጠቅ ሳይሆን በስርዓት ይማራሉ፡፡
መቼም በውጭ በኖር ብቻውን እውቀት ሊጨምር ወይም ዶላር የሰበሰበ ሁሉ ምሁር ሊሆን አይችልም፡፡
የውነት እዚህ በሚያውቀውም በማያውቀውም ከሚዘባርቅ አዋቂ ነኝ ባይ ያ በሃቅ ስለሚያውቀው ነገር ብቻ የሚያወራው፣ የሚያውቀውን አውቃለው፣ የማያውቀውን አላውቅም አስተምረኝ የሚለው አርሶ አደር አዋቂ ነው ለኔ፡፡
በጣም የሚገርመው ትንሽ ክፍል የገፉ እና ጥሩ የመናገር ችሎታ ያላቸው ከሆኑማ እውቀታቸው ጥግ ከ እስከ የለውም፡፡
እንደየመድረኩ ባህሪ እና እንደ የተቃውሞው ይዘት ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ሁሉ ይሆናሉ፡፡
አንድ ሰው ብቻውን በተለያዬ አጋጣሚ የሚዲያ ባለሙያ ሆኖ ስለ ነጻ ፕሬስ፣ ስለ ምርጫ፣ ስለ ወታደራዊ  ጉዳዬች፣ ስለ ነጻነት፣ ስለማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዬች ያልተጻፈ ጥናታዊ ጽሁፍ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
በቃ ዋናው ነጥብ በየትኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ ማንም ምን ያቅርብ ኢህአዴግን የሚሳደብ እስከሆነ ድረስ በአኩራፊው መንድር እና ስብስብ ውስጥ ድስኩሩ ሚዛን የሚደፋ ነው፡፡ ምሁራዊ ተደርጎም ይታሰባል፡፡
ሳይማሩ የተማሩትን ለመተቼት መሞከር፣ ሳያውቁ የሚያውቁትን ለማረም መነሳት እና አንዳች አይነት የተሰለቼ መረጃ በመቀባበል አዋቂ መስሎ ለመታየት መሞከር እዚህም እዚያም የሚያጋጥመን እውነት ነው፡፡
ለወለደው ልጅ በቂ ምላሽ ለመስጠት የማይችል አባት፣ አመለቻሉንም የሚሸሽ በራስ መተማመን የጎደለው ሰው ድንገት ከመሰሎቹ ጋር ሲቀላቀል ለአዋቂነት በማስመሰል መንገታገቱ ምናልባት የውስጡን ጭንቀት ለማስታመም ይሆን? ወይም በትወናው የተካኑበት ከሆኑ ደግሞ የቀድሞ ስራቸው እንዳይረሳባቸው ታዳሚ ሰብስበው እያስመሰሉም ይሆናል፡፡ ልዬነቱ ይህ ቲያትር ተብሎ አለመታየቱ ካልሆነ በስተቀር ማለት ነው፡፡
በውስጡ የተፈጠረበትን መሃይምነት ለማምለጥ የሚቀላምደው አስመሳይ ሁላ መጀመሪያ ካካባቢው ቀጥሎ ከሌሎች ብሎም ራሱን በተለያዬ መንገዶች ሊያስምር ይገባል፡፡
ሰሞኑን የምሰማው ወሬ ደግሞ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ ያው መነሻው ማለቴ የወሬው ጠንሳሾችም ሆኑ አራጋቢዎች ይህንን ሲያደርጉ ችግራቸው ምን እንደሆነ ከላይ ባነሳሁት ምክንያት እረዳዋለሁ፡፡
ያው ዋነኛ ምክንያታቸው ማህይምነታቸው እና አላዋቂነታቸው ነው፡፡
አቶ ሳሙኤል ዘ ሚካኤል የተባለ ግለሰብ የፈጸመውን የማጭበርበር ድርጊት መቼም ሁላችሁም ሰምታችሁታል፡፡ ራሱን ዶክተር ኢንጅነር አድርጎ ለዓመታት ህዝብንም መንግስትንም ሲያታልል መኖሩን በማስረጃ አስደግፎ ሚዲያው ሲያነሳ ሲጥለው የሰነበተው ጉዳይ ነው፡፡
ይህንን ተከትሎ በዲያስፖራው ውስጥ የመዋለ ህጻናት ተማሪ ልጆቻቸውን ጥያቄ እንኳን ባግባቡ መመለስ የማይችሉት መሃይማን፣ ከሰላምታ በማታልፈው መግባቢያቸው ነጭ ሲያዬ በኩርፊያ ፊታቸውን የሚያዞሩት እነዚያ በተለመደ ስድነታቸው ኢትዬጵያ ውስጥ ያለውን ዲግሪ በሙሉ በሃሰት አድርገውታል፡፡
በተለይ የአመራሩ ዲግሪማ ልክ ሳይለፋበበት የተገኘ እንዲያውም እረ የውሸት ነው ሁሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አንድ ሳሙኤልን ከሚሊዬኖች ጋር የሚያነጻጽር ትንታኔ ነው እንግዲህ የዲያስፖራው ተንታኞች የሚያቀርቡት፡፡
ያን ሃገር እየገነባው ያለው አመራር እና ህዝብ እንዳልተማረ ትምህርቱም ውሸት እንደሆነ እድርጎ የሚያቀርብ ያው ያልተማረ ሰው ካልሆነ በስተቀር ማንም ሊሆን አይችልም፡፡
ለነገሩ የነዚህ ሰዎች አለመማራቸው ወይም አለማወቃቸው አይደለም ትልቁ ችግራቸው፣ መሃይምነትም በራሱ ትልቅ ችግር አይደለም፡፡ ሁለቱም በትምህርት እና በጥረት ሊቀየር የሚችል ጉዳይ ነው፡፡
ትልቁ ችግር ግን አለማወቅን አለማወቃቸው በራሱ ሁልጊዜ ከስህተት የማይጸዱ እና ከራሳቸው ጋር የሚጋጩ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ባዶ ሆነው ሙሉ ለመምሰል የሚጥሩ! በተለይ ደግሞ አዋቂ ነን ብለው ሌሎችንም ለመምራት የሚሞክሩት ብዙ ናቸው፡፡
የመሃይም ጩኸት  ባይደመጥና ባይሰማም ደንቁሮ ያደነቁራል፡፡ በዚህ የደንቆሮ ጩኸት ብዙ ሃገር ወዳድ ዲያስፖራዎች ሊረበሹ እንደሚችሉ አያጠራጥርም፡፡
ይሉኝታም፣ ግብረ ገብነትም ስለሌላቸው ሳያውቁ አወቅን ብለው አፋቸውን ሲከፍቱ ጩኸታቸው ለሰሚው ደባሪ ነው፡፡
አቦ አትደብሩን ትንሽ እውነት እውነቱን ለማወቅ ሞክሩ፡፡
ለሃገር የሚበጅ ምንም ነገር እንደሌላችሁ ባለፉት በርካታ አመታት ስራችሁ አሳይታችኋል፡፡ በተለያዬ አጋጣሚዎች የሚሰማው ድንፋታችሁም ቀደም ሲል እንዳልኋችሁ ምን ያህል ደደቦች እንደሆናችሁ የሚያሳይ ነው እና ተውት፡፡
መጀመሪያ ስነ ምግባር - ኢትዬጵያዊ ስነ ምግባር ያስፈልጋል፡፡ ከሰውሞ ከራስ ጋርም ለመደማመጥ ትንሽ መሰረታዊ እውቀት እና ግንዛቤ ያስፈልጋል፡፡
ከመሰሎቻችሁ ጋር ብቻ በጩኸት መግባባት ሰውኛ ባህሪ አይደለም፡፡ ትርጉም በሌለው መጯጯህ የሚግባቡት እንስሳት ብቻ ናቸው፡፡
አሊያ የሰው እጅ ከማየት ውጡና ስሩ፡፡ እውቀት ማለት ፖለቲካ ወይም ታሪክ ምናምን ብቻ አይደለም ስራ መቻልም ሰርቶ መብላትም በራሱ እውቀት ነው፡፡


03040995
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
1079
1650
42108
51980
3040995

Since April 1, 2014

Photo Gallery