You are here: HomeARTICLESተመራጭ፣ ታጋይና ልማታዊ - የትላንትና ዛሬ የቤተሰብ ወግ

ተመራጭ፣ ታጋይና ልማታዊ - የትላንትና ዛሬ የቤተሰብ ወግ Featured

Published in Articles
Rate this item
(4 votes)

በዚህ ወግ የምናወጋው በሃገር ማነጽ ተግባር በዘመን እና በርእዬት አለም ሳይገደብ የድርሻውን ያበረከተን የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ነው፡፡
ታሪክ ሂደት እንደመሆኑ በዚያ ሂደት ውስጥ የሚቀያየረው ያስተሳሰብ እና የአስተዳደር ስርዓት የሚፈጥራቸው በዘመን ሂደት የሚፈጠሩ በርካታ ክዋኔዎች ይኖራሉ፡፡
ሃገሩን እና ህዝብን ማእከል ባደረገ መርህ የሚመራ በተሰብ ይሁን ግለሰብ ግን መርሁ እና አስተሳሰቡ ሁሌም ልክ ነውና ተግባሩ ከትላንት ተሸግሮ ለዛሬም የሚዘከር ይሆናል፡፡
ከላይ በምስሉ ላይ ያየናቸው ቀኛዝማች ገብረ እግዚአብሔር አብርሃ በንጉሱ ዘመን በአድዋ አካባቢ ለህግ መወሰኛው ምክር ቤት ተመርጠው ህዝባቸውን ያገለገሉ ሰው ናቸው፡፡
እኝህ ሰው በዘመናቸው የቻሉትን ያህል ለሃገራቸው ጥቅምና ህዝብ ማገልገላቸው ብቻም አይደለም ትልቁ ቁም ነገር፡፡ ቁም ነገሩ ከራሳቸውም ባሻገር የሃገር እና የህዝብ ፍቅራቸውን ለወገናቸውም ያስተላለፉበት መንገድ ጭምር ነው፡፡
ለነገሩ በምርጫ ሰበብ ረብሻና ብጥብጥ እንዲነሳ ለሚጥሩት የዛሬ የውሸት ዴሞክራሲያዊያን ነን ባዬች የያኔውም የነቀኛዝማች ምርጫ ሂደቱም ቢሆን የሚያስተምራቸው ነገር ሳይኖር አይቀርም፡፡
ምክንያቱም ጣትን በምልክትነት ቀስሮ የሰው አይን ለመጠንቆል የሚወዳደር አካል ዘመን ወደ ኋላ ተመልሶም ቢሆን ሊማር ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡
ከግማሽ ክለ ዘመን በፊት እነ ቀኛዝች ገብረእግዚአብሔር ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቀሙበትን አባባል እንደ ወረደ ላስነብባችሁና የአላማ ጽናቱንም ሆነ ግብረ ገብነቱን ለአንባቢ ግንዛቤ እንተወው፡፡ እግረ መንገዱንም ከስድብ እና ከጥላቻ ውጭ አጀንዳ ሳይሆራቸው ለሚርመሰመሱት የዘመኑ  ተቃዋሚወች አንዳች የሚያስተምረው ቁም ነገር ሳይኖረው አይቀርም፡፡


    “የህግ መምሪያ ምክር ቤት አማካሪ የህዝብ እንደራሴ ሲፈለግ ….ያገሩን ታሪክ አጣርቶ የሚያውቅ፣ አስፈላጊውን በጊዜው የሚያሳስብ፣ በግብረ ገብነት የተመሰገነ እንዲሆን አስፈላጊ መሆኑን በሁሉ የታወቀ ነው፡፡
    ጠቅላላው የሃገሪቱንና የህዝቡን ኑሮ እድገት የሚሻሻልበትን በእርሻ፣ በልዬ ልዬ ፋብሪካዎች አገሪቱን እንድትበለጽግ የምትዳብርበትን ዘዴ በብራርቶ የሚገልጽ እንደራሴ ይጠይቃል፡፡
    ከሁሉ አስቀድሞ ለህዝብ ጤናና ትምህርት አስፈላጊ ሁነው ስለተገኙ፣ ህክምናና ትምህርት ትምህርት ቤቶች በየቀበሌው እንዲቋቋሙ የሚያሳስብ እንደራሴያችሁ  ይፈለጋል፡፡
    በገበሬዎቹና በነጋዴዎቹ በኩል ያለው የግብር አከፋፈል በቅርቡ ሆኖ የሁሉን መጠን የሚያውቅ አስተዋይ እንደራሴ መምረጥ የግድ ይሆንብናል፡፡
    የቤተ ክህነት፣ የመንግስት ወታደሮችና የሲቪል ሰራተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ የሚያስረዳ እንደራሴ ያስፈልጋል፡፡
    ያገሩን ወግና ህግጋት ከዘመናዊው ስልጣኔ ጋር በማስማማት እንዲራመድ ሃሳቡን የሚያቀርብ እንደራሴ መምረጥ ለዘመኑ ጠቃሚ፣ ለታሪክ ቅርስና ብልጽግና ሊያስደኝ ይችላል፡፡
    ህዝብ ሆይ፤
    ከዚሁም ሌላ የህዝብ እንደራሴዎች የሚያመነጯቸው ደንቦችና ህጎች በሺ የሚቆጠሩ መኖራቸው የታመነ ነውና እንዳስፈላጊነቱ ሰፊ ሃሳብ በመስጠትና በመቀበል በታማኝነት የሚያገለግላችሁ ዋስትና ያለው እንደራሴያችሁ፣
ቀኛዝማች ገብረእግዚአብሔር አብርሃን ምረጡ”


እንግዲህ እንዲህ ያለው የምርጫ ቅስቀሳ በትንሹ አንድ ነደር ያመላክታል፡፡ እድገትና ስልጣኔ መሻትን፣ የሃገር ፍቅርን እና ወገናዊነት እንዲሁም ከሁሉም በላይ ተመራጮች ወደ ምርጫ ሲመጡ ግልጽ አላማና እቅድ እንዳላቸው በቀደመው ዘመን እንዲህ ይሰራ እንደነበር ያሳያል፡፡
ዛሬ ሰልጥነናል አድገናል በምንልበት በዚህ ወቅት ግን ምንም ግልጽ አላማና ፕሮግራም ሳይኖራቸው የፖለቲካ ስልጣን ለመጨበጥ እና ህዝብ እንመራለን ሲሉ የምነሰማቸው አንዳንዶች ግን ከዚህ ቢማሩ መልካም ነው እላለሁ፡፡
ቀደም ሲል ወዳነሳሁት ሃሳብ ስመለስ ቤተሰብ የሃገር ፍቅር እና የሃቀኝነት መነሻ መሆኑን ለማሳት የቀኛዝማች ገብረ እግዚአብሔር አብርሃን አስተምህሮ እና መስዋእትነት ማንሳት ወደድሁ፡፡
ደርግ በስልጣን ዘመኑ ህዝብን እንደ ህዝብ ሀገርን እንደ ሃገር በሚጨቁንበት በዚያ ዘመን ጭቆናን ለመታገል ራሳቸውን አሳልፈው ከሰጡ እልፎች መካከል የቀኛዝማች ቤተሰቦችም ይገኙበታል፡፡
አስፈሪውን የጭቆና አገዛዝ በሞትና በህይወት መካከል ሆነው በቁርጠኝነት እንዲታገሉ ልጆቻቸውን መርቀው የሸኙ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡
እኝህ ሰው ለአቅመ ትግል የደረሱትንም ልጆቻቸውን በሙሉ ወደ በረሃ ለነጻነት እንዲታገሉ በዚያ ቀውጢ ሰዓት ሲልኩ ምክንያታቸው ቀደም ሲል ያነሳነው ወገናዊነት እውነትን፣ ፍትህንና ርትእን መሻት ነው፡፡
በዚህም የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን በመስዋእትነት አጥተዋል፡፡
እንግዲህ ከህዝብ እንደራሴነት እስከ ነጻነት ትግል የቀጠለው የዚያ ቤተሰብ አቋም በልጆቻቸው እና በብዙ እልፍ ወጣቶች መስዋእትነት የነጻነት ጎህ ሲቀድ እና ሰላምና መረጋጋት ሲመጣ ቀጣዬ ትግል ከድህነት ጋር መሆኑ ሲታወጅ የዚያ ቤተሰብ የአስተሳሰብ ውጤት ደግሞ በልማታዊነት ቀጠለ፡፡
ቀኛዝማች ገብረ እግዚአብሔር አብርሃ ልጅ አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ወንድሞቻቸውን እና እህታቸውን በመስዋእትነት ማጣታቸው የፈጠረባቸው ብቸኝነት ከስኬት ጎዳና አላስቆማቸውም፡፡
አቶ ዳዊት ባደጉበት የጥንካሬ እና የአላማ ጽናት ተነሳስተው ለውጤት እንደበቁ በልበ ሙሉነት ይናገራሉ፡፡
አቶ ዳዊት በተለያዬ የአለም ሃገራት ሰርተው ያካበቱትን ዘመኑና ጊዜው በሚጠይቀው የእድገት ትግል ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የሃገራቸውን ልማት ለማፋጠን መዋእለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ካሉ ባለሃብቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
በውጭ እንደመኖራቸው የውጭውን ተሞክሮ ከሃገራቸው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር በማጣጣም በቅርበት የወገናቸውን ችግር ለመፍታት ተጠቅመውበታል፡፡
ተወልደው ባደጉበት አካባቢ ለአካባቢው ወጣቶች የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶችን እገነቡ የሚገኙት አቶ ዳዊት ሰርተው ያካበቱትን ሃብት ሃገራቸው ላይ ኢንቨስት የማድረግ ጽኑ ቁርጠኝነት አላቸው፡፡
ለዚህም ነው የራያ ቢራ አክሲዬን ማህበር በሁለት እግሩ እንዲቆም ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት፡፡
በነገራችን ላይ አቶ ዳዊት ራያ ቢራ በሚቀጥለው አመት እውን እንዲሆን የ1.6 ቢሊዬን ብር አክሲዬን በመግዛት ለልማቱ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡ በዚህም ከራያ ቢራ አክሲዬን ማህበር የ25 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡
“ሃገሬ ላይ ኢንቨስት የማደርግበት ስራ ለበርካታ ወገኖቼ ጥቅም እስካስገኜልኝ ድረስ ምንም አይነት ትርፍ ባላገኝበት አይጨንቀኝም” ሲሉ በተደጋጋሚ የሚደመጡት ባለሃብት  የታላቁ ህዳሴ ግድብን በመደግፍም በግላቸው ያደረጉት አስተዋጽኦ ሌሎችም ሊማሩበት የሚገባ ሃገራዊነት ነው፡፡
አቶ ዳዊት ለህዳሴው ግድብ የ1.1 ሚሊዬን ዶላር የቦንድ ግዥ የፈጸሙ ታላቅ የልማት አጋር ናቸው፡፡
እንደ ቤተሰብ ተመራጭ፣ ታጋይ እና ልማታዊነትን ባንድ ላይ የተጓዙትን የአቶ ዳዊት ገብረእግዚያብሄርና የአባታቸውን ቤተሰባዊ ጉዞ ስናነሳ ከእንዲህ ያለው ሂደት ሌሎችም ቢባሩ በማለት ነው፡፡
ሃገር የግለሰብ፣ የቤተሰብ፣ የማህበረሰብ፣ እና የብሄር ብሄረሰብ መሆኑን ተረድተን እንደ አንድ ጠንክረን ከጠንካሮች በቅንነት ልምድ እየወሰድን የምንተጋበት ጊዜ ላይ መሆናችን መዘንጋት የለበትም፡፡

03161102
Today
Yesterday
This Month
Last Month
All days
3022
4118
86615
75600
3161102

Since April 1, 2014

Photo Gallery